Monday, April 14, 2014
የኢትዮጵያን ወቅታዊ የፖለቲካ ሁኔታ እና የዲያስፖራውን ሚና በተመለከተ በኖርዌይ ኦስሎ ሕዝባዊ ውይይት ተካሄደ
ዲሞክራሲያዊ ለውጥ በኢትዮጵያ የድጋፍ ድርጅት ኖርዌይ
በዲምክራሲያዊ ለውጥ በኢትዮጵያ የድጋፍ ድርጅት ኖርዌይ አዘጋጅነት አፕሪል ቅዳሜ 12/2014 በኖርዌይ ኦስሎ ከተማ የኢትዮጵያን ወቅታዊ የፖለቲካ ሁኔታ እና የዲያስፖራውን ተሳትፎ በተመለከተ ታላቅ ሕዝባዊ ስብሰባ ተካሄደ:: በሕዝባዊ ስብሰባው ላይ ቁጥራቸው ወደ ሁለት መቶ የሚጠጉ በኖርዌይ የሚኖሩ ኢትዮጵያኖች ከኦስሎ እና ከተለያየ ከተማ በመምጣት በስብሰባው ላይ የተገኙ ሲሆን የግንቦት 7 የፍትህ የነፃነት እና የዲሞክራሲ ንቅናቄ አመራር አባል አቶ ቡዙነህ ፅጌ የስብሰባው ተጋባዥ እንግዳ በመሆን ሰፋ ያለ ንግግር አድርገዋል::
ሕዝባዊ ስብሠባው በኖሬጅያውያን የሰአተ አቆጣጠር ከቀኑ 15:00 እስከ ምሽቱ 21:00 ሰዓት የተካሄደ ሲሆን የዲሞክራሲያዊ ለለውጥ የድጋፍ ድርጅት ኖርዌይ ሕዝብ ግንኙነት ሀላፊ አቶ አቢ አማረ በኢትዮጵያ ውስጥ በወያኔ አረመናዊ ስርአት በጭካኔ በግፍ ለተገደሉ እና በተለያዩ አስር ቤቶች በፖለቲካ ኣስተሳስባችው ምክንያት ያለወንጀላች የሚስቃዩ ውድ ኢትዮጵያዊን ወገኖቻችን በማስብ በዚሁ ዘረኛ ቡድን አስቃቂ የኣካል ጉዳት ለተፈጸባቸው ኢትዮጵያዊን የአንድ ደቂቃ የህሊና ጸሎት በማስደረግ ስብሰባውን አስጀምረውታል::
በመቀጠለም አቶ ዮሀንስ አለሙ የዴምክራሲያዊ ለውጥ በኢትዮጵያ የድጋፍ ድርጅት ኖርዌይ ሊቀመንበር የመግቢያ ንግግር ያደረጉ ሲሆን በንግግራቸው ስለ ዲምክራሲያዌ ለውጥ የድጋፍ ድርጅት ኖርዌይ አመሰራረት እና ስለ ድጋፍ ድርጅቱ አላማ በማብራራት የድጋፍ ድርጅቱ በአሁኑ ሰአት በሀገር ቤት በሰላማዊ ትግል የወያኔን መንግስት ለመጣል እየታገሉ ያሉትን የፖለቲካ ድርጅቶችን እየረዳ እንደሚገኝ እና ከሀገር ውጭ ደግሞ የወያኔን መንግስት በሁለገብ ትግል ለማስወገድ እየሰራ ያለውን የግንቦት 7 የፍትህ የነፃነት እና የዲሞክራሴ ንቅናቄ የፖለቲካ ድርጅትን በግንባር ቀደምነት እየረዳ እንዳለ በመግለጽ የወያኔን ዘረኛ ስርአት ለመጣል ሁሉም ሰው አስተዋጿ ማድረግ እንደሚጠበቅበት እና ማንኛውም ኢትዮጵያዌ ዜጋ በሀገራችን የጋራ ጉዳይ ስለሆነው የኢትዮጵያ ወቅታዊ የፖለቲካ ሁኔታ ሀሳብ በመለዋወጥ ፣በመካከላችን ያሉትን ማንኛውንም የሃሳብ ልዩነቶች ወደ ኋላ በመጣል ፣ በመቻቻል፣ ሀገር እያፈረሰ እና ሕዝብ እያዋረደ ያለውን የዘረኛውን የወያኔን መንግስት ሁሉም ኢትዮጵያዊ በሁለገብ ትግል ለማስወገድ መረባረብ እንዳለበት አጽኖት ሰጥተው ንግግር አድርገዋል::
Ethiopians public meeting in Norway
በመቀጠለም ዲምክራሲያዊ ለውጥ የድጋፍ ድርጅት ኖርዌይ ድጋፍ ከሚሰጣቸው ድርጅቶች መካከል አንዱ የግንቦት 7 የፍትህ የነፃነት እና የዲሞክራሲ ንቅናቄ አመራር አባል የሆኑት አቶ ቡዙነህ ፅጌ የስብሰባው ተጋባዥ እንግዳ ሰፊውን ጊዜ በመውሰድ ከንጉሱ ስርአት ጀምሮ በደርግ መንግስት ዘመንም በሀገራችን የተደረጉ የፖለቲካ ንቅናቄዎችንና ለውጦችን አንድ በአንድ በመዘርዘር አሁን ካለው የወያኔ ኢህአዲግ መንግስት ጋር በማነጻጸር ሰፋ ያለ ትንታኔ ያቀረቡ ሲሆን አሁን ላይ ሀገሪቱን እየመራው ነው የሚለው የወያኔ መንግስት ከዚህ ቀድሞ ኢትዮጵያን ከመሩት ከሁለቱ መንግስታቶች ማለትም ከንጉሱም ከደርግም መንግስት ጋር ሲነጻጸር ፈጽሞ እንደማይገናኝ የወያኔ መንግስት ዘረኛና የዘረኝነት ፖለቲካ እያራመደ ያለ አረመናዊ መንግስት እንደሆነ አብራርተዋል::
የግንቦት 7 የፍትህ የነፃነት እና የዲሞክራሲ ንቅናቄ አመራር አባል አቶ ቡዙነህ ፅጌ አክለውም ከወያኔ በፊት የነበሩ ሁለቱ መንግስታቶች ለውድቀት የዳረጓቸውን ምክንያቶች በመጥቀስ የወያኔን አንባ ገነናዊ መንግስት ለአፋጣኝ ውድቀት ሊዳርጉት ይችላሉ የሚሉትን ግልጽ ምክንያቶች በመዘርዘር አስቀምጠዋል:: አቶ ቡዙነህ በሁለት የኢትዮጵያ ወቅታዊ ጉዳዮች ላይ በማንሳት እና በማብራራ ከሕዝብ ውይይት እንዲያደርጉበት ለመወያያ ያቀረቡ ሲሆን እነዚህም:
1, በሙስሊሙ ማህበረሰብ እና በወያኔ መካከል ያለው ግጭት
2, የህዳሴ ግድብን በማስመልከት ያለው ተቃውሞ
ስለሙስሊሙ ማህበረሰብ ተቃውሞ ሲናገሩ የሙስሊሙ ትግል በሁለት አመታት ውስጥ የተደረገው ሰላማዊ ትግል በጣም የተሳካና ወያኔ በቀላሉ ሊያዳፍነው ያልቻለው ሰላማዊ መብትን የመጠየቅ ትግል እንደሚያደንቁ በመናገር ነገር ይህ በሙስሊም ማህበረሰብ በኩል እየተደረገ ያለው ትግል እስከ አሁን ድረስ ከመንግስት በኩል ምንም አይነት መልስ ሊያገኝ እንዳልቻለ እና ወደፊትም ከወያኔ መንግስት በኩል ምንም አይነት መልስ ያገኛል የሚል እምነት እንደሌላቸው ተናግረዋል:: ለዚህም ማስረጃው የኢትዮጵያ ሙስሊሞች ከጠየቋቸው አራት የመብት ጥያቄዎች አንዱም ካለመመለሱ በተጨማሪ እስካሁን መሪዎቻቸውም በሃሰት ውንጀላ በእስር እየማቀቁ ያለፍርድ እየተንገላቱ መሆናቸው ነው::
ነገር ገን አሁን እየሆነው ባለው ሁኔታ በእንደዚህ አይነት መንገድ እስከመቼ ድረስ የሙስሌሙ ትግል ይቀጥላል በማለት የተናገሩ ሲሆን አሁን እየሄደ ባለው አካሄድ የሙስሊሙ ተቃውሞ የትግል አቅጣጫውን እስካልቀየረ ድረስ ረጅም ርቀትን ትግሉ ሊቀጥል ይችላል የሚል እምነት እንደሌላቸው እና ነግር ግን የሙስሊሙ ጥያቄ ከእምነት መብት ጥያቄ ባሻገር ወደ የዜግነትን መብት ወደ ማስከበር መለወጥና መሸጋገር እናደለበት በመናገር የሙስሊሙ ማእበረሰብ ጥያቄ ፍሬ ሊያፈራ የሚችለው ትግሉ በዚህ መልኩ ሲቀጥል እንደሆነ ሰፋ ያለ ማብራሪያ ሰተዋል::
በሁለተኛም የህዳሴ ግድብ በሚመለከት ያቀረቡት ሀሳብ ወያኔ የራሱን የፖለቲካ ኪሳራና በህዝቡ ላይ እያደረሰ ያለዉን ግፍ በዕድገት ስም ለመሸፈን ያመጣዉ እንጂ ታቅዶበትና ለህዝቡ በማሰብ እንዳልሆነ በኢትዮጵያና በህዝቡ ላይ እያደረሰ ያለዉ ግፍ እንደ ማስረጃነት በማቅረብ ያብራሩ ሲሆን እንደ ምሳሌም ወያኔ ሃገራዊ የሆነ አላማ ይዞ ካለመነሳቱ አንፃር የሃገርን ድንበር አሳልፎ እስከመስጠት እየሄደ ያለበትን ሁኔታ ጠቅሰው ይህ አሰራር ደግሞ የዲክታተሮች ባህሪ እንደሆነ አብራርተዋል::
የወያኔ መንግስት በህዳሴ ግድብ ሰበብ ምክንያት በማድረግ በመላው አለም ኢትዮጵያኖች በሚኖሩበት ሀገሮች በመዞር የዲያስፖራውን ቀልብ ለመውሰድ የሚያደርገው የአባይ ቦንድ ሽያጭ ሩጫ በዲያስፖራ ተቃዋሚዎች አማካኝነት በፍጹም እንዳልተሳካለት ይህንንም የወያኔ በአባይ ቦንድ ሽያጭ ስም ገንዘብ ዘረፋ በመቃወም ወያኔን አሳፍረው ከመለሱት መካከል በኖርዌይ የሚኖሩ ኢትዮጵያኖች እንደሆኑ በማስታወስ የዚህ የህዳሴ ግድብ ግንባታ ሰበብ የወያኔን መንግስት ወደ መጥፎ ውድቀት ላይ ሊጥለው እንደሚችል በማመን የወያኔ መንግስት በአሁን ሰአት ከግብጽ መንግስት ጋር እየገባ ያለው ሰጣ ገባ ለኢትዮጵያ መጥፎ ሊሆን እንደሚችል በመግለጽ ንግግራቸውን አጠቃለዋል::
በመቀጠልም አቶ ብዙነህ ባነሷቸው ነጥቦችና እና በሌሎችም ጉዳዮች ላይ ከስብሰባው ተሳታፊዎች ለቀረበላቸው በርካታ ጥያቄዎች ማብራሪያ የሰጡ ሲሆን ሰፋ ያለ ውይይትም ተደርጓል፥፥ ከውይይቱም በማስቀጠል የዲምክራሲያዊ ለውጥ በኢትዮጵያ የድጋፍ ድርጅት ኖርዌይ ምክትል ሊቀመንበር አቶ ዳንሄል አበበ የዲምክራሲያዌ ለውጥ በኢትዮጵያ የድጋፍ ድርጅት ኖርዌይ የአቋም መግለጫ ንግግር ያደረጉ ሲሆን ድርጅታቸው ወያኔ በኢትዮጵያ ሕዝብ ላይ እያደረሰ ያለውን ግፍና በደል ፈጽመው እንደሚያወግዙ እና ዴምክራሲያዌ ለለውጥ የድጋፍ ድርጅት ኖርዌይ ሁል ጊዜ ከግንቦት 7 የፍትህ የነፃነት እና የዲሞክራሴ ንቅናቄ ጎን እንደሚቆም ቃል በመግባት የአቶ ቡዙነህ ፅጌን በኖርዌይ በመገኛት ለህዝቡ ለሰጡት ገለጻ አመስግነዋል::
በዝግጅቱ መጀመሪያና ማጠቃለያ ላይ የግንቦት 7 ህዝባዊ ሃይል መዝሙር በመዘምራን የተዘመረ ሲሆን በየጣልቃው የተለያዩ የባህል ዘፈኖች በተወዛዋዦች ታጅቦ የቀረበ ሲሆን ጣእም ያለው ባህላዊ ምግብም በዲሞክራሲያዊ ለውጥ በኢትዮጵያ የድጋፍ ድርጅት ኖርዌይ የሴቶች ክፍል ተስተናግዷል፥፥ ስብሰባውን ተጀምሮ እስኪያልቅ አቶ ፍቅሬ አሰፋ መርተውታል::
በመጨረሻም የዲሞክራሲያዊ ለውጥ በኢትዮጵያ የድጋፍ ድርጅት ኖርዌይ ለዝግጅቱ መሳካት የበኩላችሁን ላበረከታችሁና ከተለያዩ የኖርዌይ ከተሞች ረዥም ርቀት በመጓዝ የዝግጅቱ ታዳሚ ለነበራችሁ ውድ ኢትዮጵያውያን እና እንዲሁም የድርጅቱ አባላቶች ታላቅ ምስጋና እናቀርባለን::
ድል ለኢትዮጵያ ህዝብ !
አንድ ባርያ ነጻ የሚወጣው መቼ ነው? ሲፈቅድ ነው? ወይስ ሲፈቀድለት? (ፕ/ር መስፍን ወ/ማርያም)
በአለፈው ሳምንት (ፋክት ቁጥር 36) ወይዘሮ መስከረም የተለያዩ መጻሕፍትን በመጥቀስ በሴቶች ላይ ያለውን መጥፎ ጫና በደንብ ያስመሰከረች ይመስለኛል፤ ግን እኮ በሴቶች ላይ ያለው ጫና የቆየ፣ ክፉና ጎጂ መሆኑን ማንም ያውቀዋል፤ ቁም-ነገሩ ያለው ከዚያ የባህል ጭነት በራስ ጥረት ወጥቶ፣ ነቀፌታንም ሆነ እርማትን ለመቀበል ሳይፈሩና ሳያፍሩ እንደመስከረም በአደባባይ ሀሳብን በመግለጽ በአገርና በወገን ጉዳይ መሳተፍና ሌሎችም እንዲሳተፉ የተቻለን ሁሉ ማድረጉ ላይ ነው፤ ለዚህ ነው ይህንን መልስ የምጽፈው፤ ወይዘሮ መስከረም በአጋጠሟትና በምታያቸው እንቅፋቶች ላይ ማተኮርዋ እንደርስዋ መንፈሳዊ ወኔው የሌላቸውን ያስፈራራቸዋል እንጂ አያበረታታቸውም፤ የማንንም አፍአዊ ጫና ተቋቁመው በራሳቸው የውስጥ ኃይል እንዲመሩ እናድርግ።Prof. Mesfin Woldemariam : is an Ethiopian Human Rights activist and philosopher
አንድ መጽሐፍን በመጥቀስ ወይዘሮ መስከረም የሚከተለውን ጽፋለች፡–
ፈጣሪ የሠራውን ውጫዊ ገጽታን ማሽሞንሞን በቂ እንደሆነ ሲነገራት የኖረች ሴት፣ በምን ተነሳሺነት አእምሮዋን የሚመግብ እውቀት ልትሻ ትችላለች? … በልጅነት እውቀትን ወደመሻት ያልተገፋ ማንነት በጉብዝና ወራት አላዋቂ በመሆን ቢወቀስ ትርጉም አይኖረውም፤ …››
ወይዘሮ መስከረም ሔዋን ሲነገራት የማትሰማ የመጀመሪያዋ ሰው (ልብ በሉ ሴት አላልሁም፤) መሆንዋን እንዴት እስከዛሬ ሳታውቅ ቀረች? ባለመጽሐፉም ይሁን መስከረም የሔዋንን ታሪክ ሳያነሡ መቅረታቸው መሠረታዊ ስሕተት ነው፤ በተጠቀሱት ሁለት ዓረፍተ ነገሮች ውስጥ አንድም እውነትን የሚመስል ነገር የለም፤ መስከረም ‹‹የሔዋን ዘር›› ከማለት በፊት የሔዋንን ሥራ ቆም ብላ ብታስታውስ የጠቀሰችውን መጽሐፍ እኔ እንደምነቅፈው ትነቅፈው ነበር፤ የሔዋን ታሪክ የሚነግረን የሚከተለውን ነው፡ ‹‹ዛፉ ለመብላት ያማረ እንደሆነ ለዓይንም እንደሚያስጎመጅ፣ ለጥበብም መልካም እንደሆነ አየች፤ ከፍሬውም ወሰደችና በላች፤ ለባልዋም ደግሞ ሰጠችው፤ እርሱም ከእርስዋ ጋር በላ፤ የሁለቱም ዓይኖች ተከፈቱ፤›› ዘፍ. 3
የሁለቱም ዓይኖች ተከፈቱ ማለት ‹‹እንደእግዚአብሔር መልካምንና ክፉን የሚያውቁ›› ሆኑ ማለት ነው፤ አሁንም ሔዋን መስከረምና ባለመጽሐፉ እንዳቀለሏት አለመሆንዋን መረዳት ይቻል ነበር፤ እንዲያውም ከዚህ በፊት እንደጻፍሁት ሔዋን የመጀመሪያዋ አብዮተኛና የነጻነት እናት ነች ለማለት ይቻላል! በአንጻሩ አዳም የፍርሃት አባት ነው፤ ‹‹ራቁቴን ስለሆንሁ ፈራሁ፤›› ያለው እሱ ነው! ስለዚህ ወይዘሮ መስከረም ‹‹የሔዋን ዘር›› የምትለውን በድላለችና ይቅርታ መጠየቅ ሳያስፈልጋት አይቀርም!
ሔዋን የተጠቀመችው ውጫዊ ገጽታን የሚያሽሞነሙን ሳይሆን የውስጥን የመንፈስ ኃይል ቆፍሮ በማውጣት ነበር፤ በዚህ የውስጥ ኃይል ለሚጠቀም ከውጭ ግፊት አይጠብቅም።
‹‹እውቀትን ወደመሻት ያልተገፋ ማንነት›› አይወቀስም፤ ትላለች ወይዘሮ መስከረም፤ እየተገፉ የሚገኘው ባርነት ነው፤ እውቀት የሚገኘው በነጻነት ነው፤ መገፋት ከእውቀት ያርቃል እንጂ ወደእውቀት አያስቀርብም፤ የመስከረም ዋናው መልእክት ሰላቢውን እንጂ ሰለባውን አትውቀስ የሚል ነው፣ ወይም የኔ ሀሳብ አህያውን ፈርቶ ዳውላውን ዓይነት ሆኖባታል፤ ለመሆኑ ሰለባ የሚሆን ከሌለ ሰላቢ ይኖራል ወይ? ሰለባ ከመሆን በፊት ሰለባ ላለመሆን መጣር አንዱ የኑሮ ዓላማ አይሆንም ወይ? ከዚህ በፊት ስለጨቋኝና ተጨቋኝ ደጋግሜ ጽፌ ነበር፤ ጭቆና የጨቋኙ ባሕርይ የሚሆነውን ያህል የተጨቋኙም ባሕርይ ይሆናል፤ ለጨቋኙ ጭቆና የሚጠቅመውን ያህል ለተጨቋኙም ጭቆና ይጠቅመዋል፤ ለጨቋኙ ጭቆና የኑሮው መሠረት የሆነውን ያህል ለሚርመሰመሱት የጨቋኝ ሎሌዎች ጭቆና የኑሮ መሠረታቸው ነው፤ እንዲህ እያለ ወርዶ ወርዶ የጭቆና ጠቃሚነት ለሎሌው ሎሌ፣ ለሎሌው ሎሌ ሎሌ … በኢትዮጵያ ምናልባትም የመጨረሻዋ የጭቆና ሰለባ ሚስት ትሆናለች፤ ወይም ልጆች ይሆናሉ! ጨቋኝና ተጨቋኝ የባሕርይ ቁርኝት አላቸው፤ አንዱ ያላንዱ አይኖርም፤ ወይዘሮ መስከረም ይህ እውነት ያልሆነበት ሁኔታ ወይም አጋጣሚ የምታውቀው ካለ ብታጋራን ደስ ይለኛል፤ ኢየሱስ ክርስቶስ ‹‹ሙታናቸውንም እንዲቀብሩ ሙታንን ተዋቸው፤›› የሚለው ኢየሱስ ክርስቶስ የሞቱትንና በቁማቸው የሞቱትን ሲያመሳስላቸው ነው! ለእኔ የሚታየኝ እንዲህ ነው።
መስከረም ብዙ ታላላቅ ሴቶችን ጠቅሳለች፤ በእስዋ ግምት ሁሉም በአባታቸው ወይም በባላቸው እየተገፉ ወደትልቅነት መድረኩ የወጡ ናቸው፤ አዙራ ብታየው የጠቀሰቻቸውን ሴቶች ገፉ የምትላቸው ወንዶች መጀመሪያውኑ በሴቶቹ ተገፍተው እንደነበረስ ሊታሰብ አይገባም? ምናልባት ከጠቀሰቻቸው ሴቶች ይልቅ መስከረም የሄለን ኬለርን ታሪክ ብታስታውስ ኖሮ መገፋትን አታነሣም ነበር፤ ሄለን ኬለር በሕጻንነትዋ ዓይኖችዋም ጆሮዎችዋም ሥራቸውን አቆሙ፤ የሄለን ኬለር የመንፈስ ጥንካሬ ከውስጥዋ አዲስና የተሻሉ ዓይኖችንና ጆሮዎችን እንድታበቅልና እንድትማር፣ ከታወቀ ዩኒቨርሲቲም የመጀመሪያዋ ሴት ምሩቅ ለመሆን እንድትበቃ አድርጓታል፤ ይህች አስደናቂ ሴት ከመቶ ሠላሳ ዓመታት ግድም በፊት ማኅበረሰቡ በሴቶች ላይ የነበረውን አጥር ሰብራ፣ ዓይኖችዋ ባለማየታቸውና ጆሮዎችዋ ባለመስማታቸው የገጠማትን እክል አሸንፋ ራስዋን ከወንዶች በላይ ለማድረግ በቅታለች።
መገፋትን የሚፈልግ ሁሉ፣ ካልገፉት የማይነቃነቅ ሁሉ፣ ሬትን ሲግቱት ይጣፍጣል እያለ የተቀበለ ሁሉ፣ ዶሮ ማታ፣ ዶሮ ማታ፣ እያሉ አታልለው እንኳን ዶሮ የለም ሹሮ ሲሉት የማይናደድ ሁሉ፣ ምኞቱ ልደግ ልመንደግ እያለ ሲነዘንዘው በአፈና ጭጭ የሚል ሁሉ ለወቀሳ ብቻ አይደለም ለውርደትም ክፍት ነው፤ ስለዚህም ተወቅሶ ከውርደት ከዳነ ወቀሳው ትልቅ አስተዋጽኦ ያደርጋል ማለት ነው፤ ዞሮ ዞሮ የሰው ልጆች ሁሉ — ሴት፣ ወንድ፣ ወጣት ሽማግሌ-አሮጊት፣ ባለሥልጣን ተራ፣ ገበሬ ነጋዴ፣ ወታደር ፖሊስ፣ አስተማሪ አስተዳዳሪ፣ ዳኛ ጠበቃ፣ ሀኪም መሀንዲስ፣ … — የፈለገውን ቢሆን ላለበት ሁኔታ ኃላፊነቱ የራሱና የግሉ ነው፤ ራሱን የሚገነባው ወይም ራሱን የሚንደው ራሱ ነው፤ ሰበብ እየፈለጉ ከዚህ ኃላፊነት መውጣት ቀላል ቢመስልም ተመልሶ እምቦጭ ነው፤ ዳገቱን ለመውጣት የሚመረውን እውነት መቀበል ያሻል።
በመጨረሻም በማናቸውም መንገድ፣ በማናቸውም ጊዜ፣ በየትኛውም ቦታ ወደቁልቁለት የሚገፉትን ወይም የሚነዱትን ‹‹እምቢ!›› ብሎ ድምጹን ያላሰማ ገደል ገብቶ ሲንፈራፈር ከራሱ በቀር የሚወቅሰው የለም፤ አቅመ-ቢስነት ከውጭ አይመጣም።
Friday, April 11, 2014
በኢትዮጵያ የመብቶች ትግሎች ሁሉ ህወሓትን ከሥልጣን ወደ ማስወገድ አቅጣጫ ያመራሉ!!!
የሙስሊም መፍትሔ አፈላላጊ ኮሚቴ መሪዎች የክስ ሂደት በበርካታ አሳዛኝ ጉዳዮች የታጀቡ ቢሆኑም የሚሰጡት ትምህርት ግን ከፍተኛ ነው። እነዚህ ወገኖቻችን “ችሎት” በተሰኘው የአገዛዙ የድራማ መድረግ በመገኘት ፍትህን ለመግደል ካባ ለብሰው “ዳኞች” ተብለው ለተኮፈሱ የአገዛዙ ተላላኪ ካድሬዎች እና ለመላው ኢትዮጵያ ሕዝብ ያደረጓቸው ጠንከር ያሉ ንግግሮች ካድሬ “ዳኞችን” አሳፍረዋል፤ ኢትዮጵያዊያንን ግን አኩርተዋል። እኚህ ወገኖቻችን ከወያኔ ችሎት ፍትህ ይገኛል የሚል ብዥታ ባይኖራቸውም መድረኩን መልዕክት ለማስተላለፊያነት ተጠቅመውበታል። በዚሁ መድረክ በአገዛዙ እጅ ከወደቁበት ጊዜ ጀምሮ እየደረባቸው ስላለው ሰቆቃ ሲናገሩ አድማጮች ሊቆጣጥሩት የማይችሉት ሐዘንና እልህ ውስጥ እንዲገቡ አድርጓቸዋል።
ወያኔ እንዲህ ዓይነቱ ጭካኔ የሚፈጽመው በሙስሊም መሪዎች ላይ ብቻ አይደለም። የህግ እውቅና የተሰጣቸው መብቶቻቸው እንዲከበርላቸው በጠየቁ ወገኖቻችን ሁሉ ተመሳሳይ ሰቆቃ ሲፈጸም ኖሯል፤ አሁን እየተፈጸመ ነው። “ኑሮ ከበደን” ያሉ ወጣቶች ተደብድበዋል። “የእርሻ መሬት አጣን” ያሉ ገበሬዎች ከያዙት ቁራሽ መሬት ተፈናቅለዋል፣ ተግዘዋል፣ ከነልጆቻቸው ለጎዳና ኑሮ ተዳርገዋል። በሀረር እና በአዲስ አበባ ከተሞች እንደታየው “ነግደን እንኑር” ባሉ ነጋዴዎች ላይ ከአቅም በላይ ከሆነ ግብር ጀምሮ በንብረታቸው ላይ እሳት እስከመልቀቅ የደረሰ አረመኔዓዊ ድርጊት ተፈጽሟል።
በዓለም ዓቀፍ የሰብዓዊ መብቶች ድንጋጌ አንቀጽ 18 መሠረት እያንዳንዱ ሰው በግሉም ሆነ በጋራ የፈለገውን ሃይማኖት የመከተልና የማስተማር፤ ያልፈለገውን ደግሞ የመተው መብት አለው። ስለሆነም የሙስሊም መፍትሔ አፈላላጊ ኮሚቴ አባላት ተግባራት በዓለም ዓቀፍ የሰብዓዊ መብቶች ድንጋጌ እውቅና ለተሰጣቸው መብቶቻቸው መከበር ያደረጉት ትግል ነው። ለወጉ ያህል “ሕገ መንግሥት” ተብሎ በሚጠራው ኢትዮጵያዊያንን ለመክሰሻነት ብቻ በሥራ ላይ በሚወለው ሰነድ ውስጥ የተካተቱ ቢሆንም ዓለምዓቀፍ እውቅና ያገኙ መብቶች ኢትዮጵያ ውስጥ ተረግጠዋል። ለእነዚህ መብቶች መከበር በጽናት የቆሙ የኢትዮጵያ ውድ ልጆች ከተራ የመንደር ካድሬና ጆሮ ጠቢ እስከ እስከ ከፍተኛው እርከን ባለ ባለሥልጣኖች ተዋክበዋል፤ ሰቆቃ ተፈጽሞባቸዋል።
ሙስሊሙ ማኅበረሰብ ለእምነት መብቶቹ መከበር እስካሁን ያደረገው ተጋድሎ የሚደነቅ ነው። የተቀናጁ እንቅስቃሴዎቹ፣ ተምሳሌታዊ የተቃውሞ ምልክቶች አጠቃቀሙ የሚያበረታታ ነው። ክርስቲያኑ ከዚህ የሚማራቸው በርካታ ቁም ነገሮች አሉ።
ከሙስሊም እንቅስቃሴና ወያኔ ይህንን እንቅስቃሴ ለማፈን እየሰዳቸው ካሉ እርምጃዎች የምንረዳው አንድ ትልቅ ሐቅ የቱን ያህል ጨዋና የሰለጠነ ቢሆን ወያኔ የሕዝብ ድምጽ ለማዳመጥ ፍላጎት የሌለው መሆኑን ነው። ሙስሊም ወገኖቻችን ጥያቄዎቻቸውን በሚያስገርም ቁጥብ ሥነሥርዓት (ዲሲፕሊን) ቢያቀርቡም ከወያኔ የተሰጠው ምላሽ ግን አፈና፣ ረገጣ፣ ቶርቸር እና ከእስከዛሬዎቹ ይበልጥ አፋኝ የሆኑ ደንቦችና ድንጋጌዎችን ነው። ሌሎች የኅብረተሰብ ክፍሎች ያደረጓቸው ትግሎችም እንደዚሁ ወደ ባሱ የመብት ጥሰቶች እያመሩ ነው። ከዚህ የምንማረው ነገር ትግሉ ውጤታማ እንዲሆን ስትራቴጂዎችን መፈተሽ እንደሚያስፈልግ ነው።
እንደሚታወቀው፤ ሰብዓዊ መብቶች እርስ በርሳቸው የተቆራኙ፤ እርስ በርሳቸውም የሚደጋገፉ ናቸው። አንዱ የመብት ዓይነት ሲጓደል፤ ሌላውም አብሮ ይጓደላል። ለምላሴ የመናገር መብት ተገፎ እያለ የማምለክ መብት ሊፋፋ አይችልም፤ ወይም ደግሞ ፍትሃዊ ዳኝነት የማግኘት መብት ተጥሶ እያለ የማምለክ መብትን የሚያስከብር ተቋም ሊኖር አይችልም።
ለመብቶች መከበር የሚደረጉ ትግሎች፤ በተለይም ደግሞ የሙስሊም ወገኖቻችን ትግል የደረሰበት ደረጃ በአንክሮ ሲጤን ስትራቴጂን በተመለከተ በጥልቀት ልናስብባቸው የሚገቡ በርካታ ጉዳዮች መኖራቸውን እንገነዘባለን። ለጊዜው ሁለት ነገሮች ላይ አጽንዖት ሰጥተን እናልፋለን።
ከላይ እንደተገለፀው የመብት ትግሎች ሁሉ መደጋገፍ ይኖርባቸዋል። ቀደም ሲል በባህርዳር፣ በኋላም በአዲስ አበባ በሴቶች ዓለም ዓቀፍ ቀን አሁን ደግሞ በደሴ ውስጥ እንደታየው የመብት ጥያቄዎች ሁሉ ተደጋግፈው መነሳት ይኖርባቸዋል። ይህ የመደጋገፍ ልምድ የሁለቱ ትላልቅ ሃይማኖቶች ተከታዮች ለየእምነቶቻቸው ነፃነት በሚያደርጉት ትግል ውስጥ መኖር ይኖርበታል። የሙስሊሞች የመብት ጥያቄዎች የክርስቲያኖችም፤ የክርስቲያኖች ደግሞ የሙስሊሞችም መሆን ይኖርበታል።
በሥልጣን ላይ ያለው የህወሓት አገዛዝ አንዱንም የመብት ጥያቄ መመለስ የማይችል መሆኑ ግልጽ መሆን ይኖርበታል። በኢትዮጵያ ተጨባጭ ሁኔታ የመብት ጥያቄዎች ግብ ወያኔን ከሥልጣን ከማባረር ያነሰ መሆን አይችሉም። ስለሆነም የመብት ማስከበር ትግል ስናካሂድ ይህን አልመን እና ለዚህም ተዘጋጅተን መሆን ይኖርበታል። ይህ ደግሞ ከፍተኛ የስነልቦና፣ የድርጅትና የስልት ዝግጅት ይጠይቃል።
ድል ለኢትዮጵያ ሕዝብ!!!
Monday, April 7, 2014
ያልዘሩትን ማጨድ ከቶ አይቻልም!
የወያኔ መንግስት የኢትዮጵያን ብሄር ብሄረሰቦች አጋጭቶ በመካከላቸው ጥርጣሬና መፈራራት አንግሶና የታሪክ ጠባሳዎችን እንደ አዲስ በመጓጐጥ እያደማ ከፋፍሎ ለመግዛት ካለመታከት ያደረጋቸው ሙከራዎች ገና ፍሬ ባያፈሩም ቁጥቋጦዎቹ መብቀል ጀምረዋል። እዚህም እዚያም በካድሬዎች የውስጥ ለውስጥ ተልእኮ የሚለኮሱ እሳቶች መብለጭለጭ ጀምረዋል። ሌላው ቀርቶ በአንድ ብሄረሰብ መሃል ሳይቀር በከባቢ ልዩነቶች ብቻ መናቆሮችና መጋደሎች እያስተዋልን ነው። ሰሞኑን በጉጂና በቦረና ኦሮሞዎች መካከል የወያኔ ሎሌዎች በሚያበረታቱት አተካሮ የብዙ ወገኖቻችን ህይወት ጠፍቷል። ሰዎች ከኑሮአቸው ተፈናቅለዋል። ወያኔ እንደኳስ ጨዋታ ተመልካች ዳር ሆኖ ይመለከታል፣ ያጨብጭባል።
ሰሞኑን ባህርዳር ከተማ ውስጥ በተካሄደ የስፖርት ውድድር ላይ አሳፋሪ ክስተት ነበር። ለሰሚው የሚቀፍ ብልግና የተቀላቀለበት ስድብና ቁርቋሶ አይተናል። ከበስተጀርባ ሆነው ይህንን ለፍቅር ብቻ ሊውል የሚገባ የስፖርት ዝግጅት መርዝ ረጭተውበታል። ከዚህ ላቅ ያሉ የተንኮል ድግሶችም ተደግሰው ህዝብ ውስጥ በወያኔ ከተነዙ የመርዝ ቢልቃቶች ውስጥ ስራ ላይ ሳይውሉ ቀርተዋል።
ይህ በታሪካችን ታይቶ የማይታወቅ ዘር የሚዘራው ወያኔ ያልተከፋፈለ ህዝብ አይገዛልኝም በሚል ፍልስፍና እንደሆነ በተደጋጋሚ እያየን ነው። ሶማሌ ክልል ውስጥ በተቋቋሙ ልዩ ፖሊስ በሚል ስያሜ በሚጠሩ የመንግስት ሃይሎች ጥቃት ቁጥሩ እጅግ በርካታ የሆነ የኦሮሞ ማህበረሰብ ከኖረበት መሬት ተጠራርጎ እንዲወጣ ተደርጓል። ብዙዎቹ ተገድለዋል። ብዙ ደም መቃበት ተፈጥሯል። በየክልሉ ምስኪን የአማራ ገበሬዎችን መሬት ንብረት በመንጠቅ አከባቢውን ለቀው እንዲሄዱ አድርገዋል። መሄጃ የለንም ያሉትንም ቀጥቅጠው እንደገደሏቸው ሰሞኑን ከጅባትና ሜጫ አካባቢ ያሉ መረጃዎችን አይተናል።
እነዚህ በየቦታው የሚብለጨለጩ እሳቶች በዚህ ከቀጠሉ ሁላችንም ወደ ሚያቃጥልና የሚለበልብ የሰደድ እሳት ማደጉ አይቀርም። የወያኔ ባለሟሎች ካለምንም ይሉኝታና ማሰላሰል ይህንን እሳት እያራገቡ ይገኛሉ።
ይህንን አደገኛ አዝማሚያ በንጭጩ ማስወገድ የሚችለው ራሱ ህዝቡና የኢትዮጵያ ዲሞክራሲያዊ የነጻነት ሃይሎች ድምጽና ህብረት እንጂ የወያኔ መንግስት አይደለም። ስለዚህ ህዝቡ በተለይም ወጣቶች ከዚህ ወጥመድ ሰብረው እንዲወጡ ግንቦት 7 የነጻነት፣ የፍትህና የዲሞክራሲ ንቅናቄ አጥብቆ ያሳስባል። ተመሳሳይ ተንኮሎችንም ማጋለጡን ይቀጥላል። የብሄርሰብ ልሂቃንም ይህንን መርዝ እንዲቋቋሙ፣ ይልቁንም ወያኔ እንዳይመቸው ይበልጥ መቀራረብና ፈተናውን በጋራ እንድንቋቋም ጥሪያችን በድጋሜ እናቀርባለን።
ያልተዘራ አይታጨድም። ወያኔ የዘራልን መርዝ የሚያፈራው መርዝን እንጂ ሌላ አይደለም። ልዩነቶቻችን እንደዘመኑ በሰለጠነ ዲሞክራሲያዊ መንገድ እንጂ በተያዘው መንገድ ማስወገድ አይቻልም።
ዞሮ ዞሮ በዚህ ሳይጣናዊ የወያኔ መሰሪ ሴራ ለምትፈስ ለእያንዳንዶ የደም ጠብታ ተጠያቂው የወያኔ ጉጅሌ መሆኑን አጥብቀን እናሳስባለን። በመሆኑም ለመከፋፈል ከመመቻቸት ይልቅ አንድነታችን በማጥበቅ የነጻነት ሃይሎችን በመቀላቀል ራሳችን እና የሀገራችንን ህልውና ከዚህ ከወያኔ የመከፋፈል መርዝ እንታደግ።
ድል ለኢትዮጵያ ህዝብ!!!
Thursday, April 3, 2014
ኢህአዴግ የአፍሪካ ቀንድ ስጋት?
አሜሪካ መለስ ከቆፈሩት ጉድጓድ ለመውጣት ወስናለች
ለአፍሪካ ቀንድ ሰላም ብቸኛ ተዋናይና ፊት አውራሪ አድርጎ ራሱን የሾመው ኢህአዴግ ለቀጠናው ስጋት እንደሚሆን ተጠቆመ። አልሸባብንና አልቃይዳን ከምንጩ እናጠፋለን በሚል ስትራቴጂ መለስ ከቆፈሩት ጉድጓድ ውስጥ ሰምጣ የነበረችው አሜሪካ ከጉድጓዱ ለመውጣት ወስናለች። ኢትዮጵያዊያን የሚያምኑትና የሚቀበሉትን መሪ በድፍረት አደባባይ የማውጣት ሃላፊነቱ “አገር ወዳድ” በሚሉ ዜጎችና የተቃዋሚ ፓርቲ አመራሮች ጫንቃ ላይ ነው።
ህወሃት ያቋቋማቸው ጥቃቅን መንግስታት ከህዝብ ይልቅ ለህወሃት የወደፊት እቅድ ታማኝ በመሆን መጓዛቸው ከቀን ወደቅን የፈጠረው ስሜት ኢህአዴግን እየበላው እንደሆነ የጠቆሙ የዜናው ምንጮች፣ ኢህአዴግ የምስራቅ አፍሪቃ የሰላም አባት ሊሆን ቀርቶ የራሱንም ችግር መፍታት ወደማይችልበት የቁርሾ ማሳ ውስጥ እንደሚገኝ አመልክተዋል።
ህወሃት “በነጻ አውጪነት” ያሰላውና፣ ይህንኑ ዓላማውን በፈለገበት ቀን ተግባራዊ ለማድረግ ያመቸው ዘንድ በየክልሉ ለጣጥፎ ያቋቋማቸውን ፓርቲዎች ሲመሩ የነበሩት አቶ መለስ በድንገት ካለፉ በኋላ ኢህአዴግ ውስጣዊ ሰላሙ መናጋቱ በተደጋጋሚ እየተገለጸ ነው። ኢህአዴግ በበኩሉ “የጓድ መለስን ውርስና ራዕይ ያለማዛነፍ እናስቀጥላለን” እያለ አገሪቱን በደቦ እንድተመራ ማድረጉ የሚታወስ ነው።
አቶ መለስ በጓዶቻቸው ቋንቋ “ተሰው” ከተባለበት ጊዜ ጀምሮ ምክትል ጠ/ሚኒስትር የነበሩትን አቶ ሃይለማርያም ደሳለኝን ለመተካት ተቸግሮ ነበር። ደህንነቱን፣ መከላከያውን፣ ፖሊስና ዋንኛ የአገሪቱን ተቋማት ጠቅልሎ የያዘው ህወሃት በቀጥታ አሜሪካ ባደረገችው ጫና ሳይወድ በግዱ አቶ ሃይለማርያምን በጠ/ሚኒስትርነት ለመሰየም ተገደደ። የስልጣን ክፍተቱን በተመለከተ አቻ ድርጅቶችና ህወሃት ውስጥ አለመግባባት ተፈጥሮ ስለነበር “ምደባ” በሚል ኢትዮጵያ በደቦ የሚመሯት አራት ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትሮች ተሰየሙላት።
ስማቸው እንዳይጠቀስ የጠየቁ አንድ የአሜሪካ ዲፕሎማት እንዳሉት አሜሪካ ስጋት የገባት ከዚህ ጊዜ ጀምሮ ነበር። መለስ እንዳለፉ ልዩ ልዑክ ወደ አዲስ አበባ በመላክ ሁኔታውን በመገምገም ስራ የጀመረችው አሜሪካ አሁን አሁን በህወሃት ስትራቴጂ የተሰራው ኢህአዴግ የምስራቅ አፍሪካ ቀንድ ዋንኛ የችግር ምንጭ ስለመሆኑ ድምዳሜ ላይ ደርሰዋል። በዚህም የተነሳ የአሜሪካ ፖሊሲ አውጪዎች ለጉዳዩ ልዩ ትኩረት በመስጠት እየመከሩበትና የመፍትሔ ስትራቴጂ እየነደፉ ነው።
“We cannot afford to lose Ethiopia” አሜሪካ ኢትዮጵያን ልታጣት አይገባም በማለት ለጎልጉል የዋሽንግቶን ዘጋቢ የተናገሩት የዲፕሎማት ምንጭ “የአሜሪካን ባለስልጣናት ኢህአዴግን በተመለከተ የሚጠቀሙት ቃልና የድምጻቸው ቃና ተቀይሯል” ሲሉ የጉዳዩን ክብደት አመላክተዋል።
በዋሽንግቶን የአሜሪካ ፖሊሲ አውጪዎች፣ የምክር ቤት አባላት እንዲሁም ሌሎች የሚመለከታቸው ኢህአዴግን አስመልክቶ ተደጋጋሚ ስብሰባ መቀመጣቸው ታውቋል። አዲስ አበባም ተወካይ በመላክ ከሚመለከታቸው ባለስልጣናት ጋር በግል እየተነጋገሩ ነው። በያዝነው ሳምንትም ለተመሳሳይ ስራ አዲስ አበባ የተጓዙ አሉ። እንደ ዲፕሎማቱ ገለጻ የህወሃት ሰዎች ውስጣዊ ችግር እንዳለ አይቀበሉም። በግል ያነጋገሯቸው የሌሎች ፓርቲ ከፍተኛ አመራሮች ግን ኢህአዴግ ውስጡ አለመረጋጋትና ስጋት የተሞላው ስለመሆኑ ማረጋገጫ ሰጥተዋል።
በኢትዮጵያ አንድ ችግር ቢፈጠር ለማረጋጋት አስቸጋሪ እንደሚሆን፣ ህዝቡ በተለይ በህወሃቶች ላይ የሚያሳየው ጥላቻ እየተካረረ መምጣቱ፣ በአገሪቱ የሚፈጸመው ያልተመጣጠነ የሃብት ስርጭት፣ አፈናውና ሌሎች የህወሃት/ኢህአዴግ ተግባራት ተዳምረው ህዝቡን ክፉኛ ማስቀየሙ ያልታሰበ ችግር ሊቀሰቅስ እንደሚችል አሜሪካ መገንዘቧን ያወሱት ዲፕሎማት፣ “ህወሀቶች የቀጠናው የሰላም ምንጮች ስለመሆናቸው ለራሳቸው ምስክርነት ለመስጠት ቢሞክሩም በተግባር የሚታየው ግልባጩ ነው” ብለዋል።
ኢትዮጵያ ላይ የተተከለው የጎሳ አገዛዝ እንደሆነ ያመለከቱት እኚሁ ዲፕሎማት “በጎሳ አስተሳሰብ የተዋቀረው ኢህአዴግ ችግሩ ከገነፈለ ሊቆጣጠረው የሚችል ባለስልጣንና መሪ የለውም። አስተዳዳራዊ ማዕከላዊነት አይታይበትም። በግል የሚወስን ባለስልጣንና ርምጃ የሚወስድ አካል የለውም” ሲሉ የስጋቱን ግዝፈት ያሳያሉ። በዚህ ሂደት ውስጥ ችግሩ ቢከሰት ምን ሊፈጠር እንደሚችል ማሰቡ አዳጋች እንደማይሆን ይጠቁማሉ። አያይዘውም “አሜሪካ ቸል ብላ ስትመለከተው የነበረውን ጉዳይ አጽንኦት ብትሰጠው አይገርምም” ብለዋል። አሜሪካ ይህንን የምታደርገው ለራሷ ስትል እንደሆነ ያልሸሸጉት ዲፕሎማት አንድ ጥያቄም ጠይቀዋል። “እናንተስ ለራሳችሁ ስትሉ ምን እየሰራችሁ ነው?” ከረጅም ፈገግታ ጋር።
አልቃይዳን ከምንጩ ማድረቅ በሚለው የመለስ ስትራቴጂ ለኢህአዴግ ግብር ስታስገባ የነበረችው አሜሪካ ግብሯን ስትገብር የኖረችው በፔንታጎን ወታደራዊ ውሳኔ መሰረት ነበር። ኢህአዴግም ግብሩ እንዳይቆምበት በአዲስ አበባ ታክሲ ላይና ህዝብ በሚያዘወትርባቸው ቦታዎች ፈንጂ በማፈንዳት ሲጫወተው የነበረውን ድራማ ዊኪሊክስ (ሹልክ ዓምድ) አምባሳደር ያማማቶን ጠቅሶ ማጋለጡ አይዘነጋም። በዚሁ መነሻ ይመስላል ኢህአዴግ የቀድሞውን ጨዋታ የመጫወት እድሉ እንዳከተመ እንደራሴ ክሪስ ስሚዝ ባደባባይ የመለስን ስብዕና በመዝለፍ ባልተለመደ መልኩ ተናግረው ነበር።
ለጎልጉል መረጃ የሰጡት ዲፕሎማት “እናንተስ” በሚል ለሰነዘሩት ጥያቄ ማብራሪያ ተጠይቀው “እኔ ኢትዮጵያዊ ብሆን አገሬን አስቀድማለሁ” የሚል አጭር ምላሽ ሰጥተዋል። አሜሪካ አማራጭ ማጣቷንም እንደ አንድ ችግር አንስተዋል።
በዲፕሎማቱ አስተያየት ላይ ገለልተኛ ወገኖችን አነጋግረናል። ያሰባሰባንቸው አስተያየቶች “አሜሪካ እዚህ ደረጃ ከደረሰች፣ ኢህአዴግም በዚህ ደረጃ ከተመደበ ተቃዋሚዎች የግል ጉዳያቸውንና ፕሮግራማቸውን ለህዝብ ውሳኔ በመተው ለመጪው ትውልድና ለአገር ሲሉ ከመቧደን በሽታ ሊፈወሱ ይገባል” የሚል ይገኝበታል።
የተቃዋሚ ፓርቲዎች ተቀናጅቶ መበተን፣ ተደራጅቶ መፍረክረክ፣ ተደላድለው መስለል በተለያዩ ወቅቶች ህዝብ ተስፋ እንዲቆርጥ አድርገዋል። የሚፎካከሩትን ፓርቲ ትተው እርስ በርሳቸው ለተራ ጉዳይ ሲሻኮቱ ዓመታት አሳልፈዋል። በዚህም የተነሳ “አማራጭ የለም” በሚል ኢህአዴግን ማንገስ ግድ እንደሆነ የጠቆሙት አስተያየት ሰጪዎች “የተቃዋሚ ፓርቲዎች ይህንን አስተሳሰብ ሰብረው አገር መምራት እንደሚችሉ የሚያረጋግጥ ህብረት መፍጠር ይገባቸዋል። ይህም ካልሆነ የርስ በርስ ውዝግባቸውን ማቆምና የራሳቸውን የቤት ስራ መስራት ላይ ማተኮር ግዳጃቸው ይሆናል” ብለዋል።
ምሁራን ከተደበቁበት ሊወጡ እንደሚገቡም ያሳሰቡ አሉ። አገር የመምራት፣ በህዝብ የመታመን፣ የህዝብን ይሁንታ ማግኘት እንችላለን የሚሉ ከፊት ለፊት፣ አሁን ከፊት ያለውን ችግር በመጥረግ የወደፊቷን ኢትዮጵያ በመገንባትና መጪውን ትውልድ በማዳኑ ስራ አጋዥ ሃይል ለመሆን መወሰን እንደሚገባቸው በመግለጽ ጥሪ አቅርበዋል። ከሁሉም በላይ ግን “አሁን ካለው ህዝብን ካገለለ ዘመናዊ የመሳፍንት ስርዓት ኢትዮጵያንና ህዝቧን ማሻገር የሚችል ሞገሰ ሙሉ፣ ቅን፣ ከጥላቻ የጸዳ፣ ከሥልጣን ይልቅ የወደፊቷን ኢትዮጵያ አሻግሮ መመልከት የሚችል መሪ ወደ ፊት ወጥቶ በግልጽ ለህዝብ የሚተዋወቅበትን መንገድ የማህበራዊ ሚዲያዎች፣ ድረገጾች፣ ሬዲዮኖች አገር ወዳድ የመገናኛ አውታሮች አጀንዳ አድርገው ሊወያዩበት ይገባል” የሚለው አስተያየት ሚዛኑን የደፋ ሆኗል።
Wednesday, April 2, 2014
ኢትዮጵያ ውስጥ የመገንጠል ጥያቄ ማንሳት ይቻላልን?
ይህንን ጥያቄ ከመመለሳችን በፊት በቅድሚያ ሀገር ማለት ራሱ ምን ማለት ነው? እንዴትስ ትፈጠራለች? የሚሉትን ጥያቄዎች መመለስ ይኖርብናል፡፡ ሀገር ማለት በአንድ ጥላ ስር የሚኖርባት ትልቅ ቤት ማለት ናት፣ ሀገር ማለት ጋርዮሽ ማለት ናት፣ ሀገር ማለት ከመንደር ከቀየ የገዘፈች የጋራ ጥቅም የፈጠሩ ሕዝቦች የራሳችን የግላችን የሚሉት የተከለለ ምድርና በውስጡ ያሉ ሁሉ ነገሮች ማለት ናት፡፡
ሀገር እንዴት ትፈጠራለች?
ሀገር በሦስት መንገድ ትፈጠራለች
የተለያየ ቋንቋ ባሕል ሃይማኖት ወዘተ ያላቸው ሕዝቦች በመልክአ ምድር አቀማመጥ በአየር ንብረት መመሳሰልና ተጽዕኖ ሊጋሩት በሚፈልጉት ወይም በሚገደዱት የተፈጥሮ ሀብት አጣማሪነት በስምምነት ትፈጠራለች፡፡
የጋራ ጥቅም ባላቸው ወይም በፈጠሩ አንድ ዓይነት ቋንቋ ባሕል ሃይማኖት ወዘተ ባለው ሕዝብ ያንን የጋራ ጥቅም ለራሳቸው ብቻ ለመጠቀምና ከሌሎች ለመከላከል ባላቸው ጽኑ ፍላጐት ትፈጠራለች፡፡
በኃያላን ገዥዎች ወይም ብሔረሰቦች ፍላጎት አቅማቸው በፈቀደላቸው መጠን ጥቅማቸውን ለማስከበር ለራሳቸው ለማድረግ በጣሩት መጠን ልክ ትፈጠራለች፡፡
እንግዲህ በዓለማችን ያሉ ሀገራት በዚህ መልኩ ሲፈጠሩ በተፈጠሩበት መልክም እንደገና ከውስጣቸውም ሌላ ሀገር ሲፈጠር ማለት እየፈረሱ ሲሠሩ አሁን ካሉበት ደረጃ ደርሰዋል፡፡ ከሀገራት መፈጠር የሚቀድመው ግን የጎጥ መፈጠር ነው፡፡ ፍላጎትና አቅም ከጎጥ ሲያልፍና አስተሳሰብ እየሰፋ እየጎለመሰ ሲሄድ ጎጥ ትጠበዋለች በሂደቱም ሀገር ትወለዳለች፡፡ በመሆኑም ሀገር የሥልጣኔ ፍሬ ናት ማለት ነው፡፡ የሆነ ሆኖ እንደ ዓለማዊ ተረክ ከሰው ልጅ ታሪክ አንፃር ካየነው ሀሳቡ ከ 10ሽዎች ዓታት በፊት የነበረ ሆኖም (አንድ ዓይነት ዝርያ ያላቸው ኅብረተሰቦች ሥፍራቸውን ከሌሎቹ የመጠበቅ የመከላከል ድርጊቶች ነበሩና) መልክና ቅርጽ እያየዘ የመጣው በዚሀ ዘመን ነው ለማለት እጅግ የሚያስቸግርና ምድር በአራቱም ማዕዘናት በሰው ልጆች ከመሞላቷ በኋላም የቀጠለ አሁንም ድረስ ያልተጠናቀቀ ሁልጊዜም አዲስ የቤት ሥራ እየሆነ አንድ ዓይነት መግባባት ላይ ለመድረስ ያልተቻለበት ጉዳይ ነው፡፡ ይሄም ሆኖ ከጥንት ከመሠረት ጀምሮ የሚታወቁ ሀገራት አሉ እንደ ዓለም ታሪክና መንፈሳዊው ተረክ ስናይ ኢትዮጵያ ከጥንት ጀምሮ ከተመሠረቱ ህልው ከሆኑ ሦስት ሀገራት አንዷ ናት፡፡ በዚህ ዙሪያ የተለያዩ ተረኮች አሉ፡፡
አንደኛው ኢትዮጵያን የመሠረታት የአዳም ልጅ አሪ ወይም አራም ዓለም በተፈጠረ በ 970ዓመት ነው፡፡ የመጀመሪያ ንጉሷም እሱ ነው እስከ የጥፋት ወኃ ድረስ 21ነገሥታት ነግሠው ለ 1286ዓመታት ኢትዮጵያን ገዝተዋል የሚል ተረክ ለብቻው አለ፡፡ ከጥፋት ውኃ በኋላም ኖኅ ዓለምን ለሦስቱ ልጆቹ ሲያከፋፍል አፍሪካ ለካም ደርሳው ነበርና ኢትዮጵያ ውስጥ ከነገሡት የነገደ ካም ነገሥታት የመጀመሪያው ካም ነው ብለው ከካም የሚጀምሩ አሉ፡፡ አይ አይደለም ከካም ሦስተኛ ትውልድ 2545 ዓመት ቅ.ል.ክ ከሰብታህ ነው የሚጀምረው ብለው ከሰብታህ የሚጀምሩም አሉ፡፡ በዚያም ሆነ በዚህ ሀገሪቱ ጥንታዊትና በሀገር ደረጃ በቀዳሚነት ከተጠሩ ሀገራት አንዷ ናት፡፡ በጥንት የዓለም ታሪክ መጻሕፍትም ሆነ በመንፈሳዊ መጻሕፍት ዛሬ አፍሪካ ብለን የምንጠራውን እንዳለ ኢትዮጵያ ነበር የሚሉት፡፡ በጥንቱ የአውሮፓዊያን የዓለም ካርታ ላይ አትላንቲክ ውቅያኖስን “የኢትዮጵያ ውቅያኖስ” ሲል ይጠራዋል፡፡ በሌላ በኩል ማሊ፣ ቻድ፣ ኒጀር ወደታችም ታንዛኒያ በሌሎች በተለያዩ የአፍሪካ ሀገራትም ምንጫቸው ኢትዮጵያ እንደሆነ የሚናገሩ በርካታ ማኅበረሰቦች አሉ፡፡ ባሕር ተሻግረን እስክ ቻይና የባሕር ጠረፍ ድረስ እንደገዛንም የዓለም ታሪክ ይናገራል፡፡
ከዚህ ከዚህ የምንረዳው ኢትዮጵያ ምን ያህል ረጅም ታሪክና ሰፊ ግዛት ዕውቅና የነበራት መሆኗን ነው፡፡ ባጠቃላይ ሀገራችን ኢትዮጵያ መጀመሪያ ኩሽ (በካም ልጅ ስም) ዓረቦች ወደ አፍሪካ ከመግቦታቸው በፊት ግብጽ ይኖሩ በነበሩት ጥቁር ሕዝቦች ዘንድ ደግሞ ቶ ኔቶር(ሀገረ እግዝአብሔር) ከዚያ አቢሲኒያ (በንጉሥ አቢስ ስም) ከዚያ ኢትዮጵያ (በንጉሥ ኢትዮጵ ስም) በእነዚህ ስሞች እይተጠራች ኖራለች፡፡ በዚህ እረጂም ጊዜ የቆዳ ስፋቷ ይስፋም ይጥበብ ያልተለወጠ ነገር ቢኖር ማዕከሉ ነው፡፡ የዚህ እጅግ የረጅም ዘመን አገዛዝ ወይም አስተዳደር ዓባይንና ምንጩን ጣናን እንብርት ማዕከል ያረገ ነበርና፡፡ አፍሪካ ኢትዮጵያ ከሚለው የተለየ ስም ለመያዟና አሁን በምናያቸው ሀገራት ብዛት ለመከፋፈሏ አስቀድሞ የዓረቦች ወደ አፍሪካ መግባት ወደ ኋላ ደግሞ የአውሮፓ ቅኝ ገዥዎች ቅርምት ድርሻ ከፍተኛ ነው፡፡
እንግዲህ ኢትዮጵያ እንዲህ እንዲህ እያለች እየጠበበች እየጠበበች መጥታ በከፍተኛ መሥዋዕትነት አሁን ያላትን ገጽታ ብቻ ይዛ ልትገኝ ችላለች፡፡ እንደሚታወቀው ይሄንንም ቢሆን ለማፈራረስና የሀገሪቱን ህልውና ፍጻሜ ላይ ለማድረስ ከውጭና ከውስጥ ምን ያህል እያሰፈሰፉ እያቆበቆቡ እንደሆነ ይታወቃል፡፡
ኢትዮጵያን ለመገንጠል የሚፈልጉ አካላት የፍላጎታቸው መንስኤ ምንድን ነው?
በእኔ እምነት ለዚህ ጥያቄ መንስኤ ሊሆኑ የሚችሉት ጉዳዮች ሦስት ናቸው
ጭቆናና በደል ይደርስብናል ከሚል ቅሬታ
ከራሳችን አልፎ ለተቀረው የሚተርፍ ሀብት አለን ይሄንን ሀብት ለብቻችን ማድረግ ብንችል የበለጠ ተጠቃሚ እንሆናለን ከሚል የተሳሳተ እምነት
ቅጥረኝነት(ባንዳነት) ሀገርንና ወገንን ከድቶ ለጠላት ጥቅምና ዓላማ ማደር ናቸው፡፡
የእነዚህ መንስኤዎች ተጨባጭነት ምን ያህል ነው?
የመጀመሪያውን መንስኤ ስናይ በእርግጥ በሀገራትን ጭቆናና በደል አልነበረም ማለት ፈጽሞ አይቻልም፡፡ ተጨባጩና የሚያሳዝነው ነገር ቢኖር ግን ኢትዮጵያ ውስጥ በሕዝብ በብሔረሰብ ደረጃ ተጨቆነ ተበደለ ተረገጠ ተበዘበዘ የሚባል ሕዝብ ካለ የአማራን ሕዝብ ያህል ኢትየጵያ ውስጥ እንዳልነበር ታሪካችንን ስንፈትሽ የአማራ ገበሬ በነገሥታቱ ዘመን ያሳለፈውን ሕይዎት ስናይ የምንረዳው ሀቅ ነው፡፡ የዚህ ምክንያቱ እንደ አለመታደል ሆኖ ሀገሪቱ ከጥንት ጀምሮ ለጦርነት የታደለች ሀገር ከመሆኗ ጋር ተያይዞ የአማራ ሕዝብ ለነገሥታቱ በቅርብ ርቀት ከመገኘቱና ይሄንን የመንግሥት ሥርዓት ከማስቀጠል ኃላፊነትና ግዴታ አንፃር ለሚያጋጥሙ ጦርነቶች ልጆቹን ከመገበር አልፎ ሠራዊቱ ደሞዝ አልባ ነበርና ይህ ሕዝብ ለመንግሥት ከሚሰጠው ግብር በላይ በየመንግሥት ታጣቂው በዘፈቀደ እንደተፈለገ እየተዘረፈ የመመገብ ግዴታን ሲያስተናገድ የነበረ ስለሆነ ነው፡፡
ይህ ድርጊት በሀገራችን ብቻ የነበረ ሳይሆን ተመሳሳይ የመንግሥት ሥርዓት በነበረባቸው ሀገራትም የነበረ ድርጊት ነው፡፡ የአማራው ሕዝብ በዚህ ዓይነት ግዴታ የማለፉ ውጤት አሁን ላይ የኢትዮጵያን ገበሬዎች ሕይወት ተዘዋውረን ስናይ ከሌሎቹ ብሔረሰቦቻችን ይልቅ የአማራ ገበሬዎች ሕይወት እጅግ በሚያሳዝንና ልብን በሚነካ የድህነት ዓይነት የሚኖሩ እንዲሆኑ አድርጓል፡፡ የአማራ ገበሬ በፍጹም ጥሪት መቋጠር የሚችልበትን ዕዳል አግኝቶ አያውቅም ሁለ ነገሩን ለሀገሪቱ ህልውና ለነጻነቱ ከፍሎታል፡፡ ከመኖሪያ ቤቱ አቅም እንኳን ብታዩ የአማራ ገቤሬዎች ቤቶች ከሌሎቹ ብሔረሰቦች ገበሬዎች ቤቶች የደከመና ደሳሳ ነው፡፡ በአንጻሩ የሌሎቹ የደረጀና ጥብቅ አቋም ያለው ሆኗል፡፡ ልብ በሉ እያወራሁ ያለሁት ስለ አማራው ሕዝብ እንጂ ስለ አማራ ነገሥታት አይደለም፡፡ ምንም እንኳን ጥቂቶች የሳቱ የብሔረሰቡ አባላት ብለዋልና ብየ ይህ የመገንጠል ጥያቄ የኦሮሞን ሕዝብ የወክላል ባልልም ለምሳሌ የኦሮሞን ሕዝብ ወይም ገበሬዎች ሕይዎት ብንመለከት ከአማራ በእጅጉ የተሸለ ሆኖ እናገኘዋለን፡፡ በቅርቡ በደናቁርት ተሳዳቢ የወያኔ ባለ ሥልጣናት እንደተገለጸው የአማራ ገበሬዎች ሕይዎት እኮ በ 21ኛው መቶ ክፍለ ዘመንም እንኳን ቢሆን ጫማ ለማድረግ ያልታደለ ኅብረተሰብ ነው፡፡ የልብሱም ነገር እንደዚያው ነው፡፡ ምን አለፋቹህ ባጠቃላይ ለዚህች ሀገር እራሱን የሰዋ ሕዝብ ነው፡፡
ታዲያ ለሀገር ሲል በከፈለው ዋጋ ለችጋር መዳረጉ ሊያስመሰግነው እንጂ ሊያስነቅፈው ሊያዘልፈው ይገባ ነበር እንዴ? ለችግር ቢዳረግም ነጻነትን ያህል በምንም ሊገዛ ሊለወጥ የማይችልን ሀብት አትርፏልና፡፡ ይሄ አኩሪ እሴት የአውሮፓ ሀገራት እንኳን የላቸውም አንዱ በሌላው የተገዛ ነውና፡፡ ይህ ሕዝብ በዚህ ትምክህት ያልተሰማው በሌላ በምን ሊመካ ይችላል? ትምክህተኛ ተብሎ መኮነኑ በምን ሒሳብ ነው አግባብነት ሊኖረው የሚችለው? ለነገሩ ያላቸውን ነው ሊሰጡን የሚችሉት የሌላቸውን ከየት ያመጡታል? ሕዝብን በፍቅር ገዝቶና አሳምኖ እንደ አንድ ልብ መካሪ እንደ እንድ ቃል ተናጋሪ በአንድ ሐሳብ አስማምቶ ለልማት እንዲነሣ ማድረጉንማ ከየት አምጥተውት? ችሎታና ሰብእናቸው አይፈቅድላቸውማ? ፍቅርና ክብር አያውቁማ? እንደ እንስሳ ቆጥረው በግዳጅ እያሰለፉ የግብር ውጣ ሥራ ያሠሩ እንጂ፡፡
ከዚህ ባሻገር ስላሉ ነገሮች ስናወራ በሀገራችን በርካታ ብሔረሰቦች የሚያቀርቡት ቅሬታ አለ፡፡ በማንነታችን እንድናፍር እንድንሸማቀቅ እንደረግ ነበር፣ እንደ ዜጋ አንታይም ነበር የሚለው ቅሬታ ወይም በደል አልነበረም አልተፈጸመም ማለት አይቻልም ነገር ግን ምክንያታዊ እንደነበር ልንገነዘብ ይገባል፡፡ በአርግጥ ዛሬ ላይ ሆነን ስናየው ፍጹም አግባብነት የሌለው ሆኖ አናገኘዋልን፡፡ ነገር ግን ይህ ከጥንት ጀምሮ የነበረ ጥቃት እንዴት ሊፈጠር ቻለ? የሚለው ጉዳይ መጤን መመርመር ያለበት ጉዳይ ይመስለኛል፡፡ ያለ ምክንያት የሚፈጸም ምንም ነገር የለምና አንዴትና ለምን የመገለል እንደ ዜጋ ያለመቆጠር ጥቃት ሊደርስባቸው ቻለ ለሚለው ቅሬታ የኦሮሞን ብሔረሰብ በተመለከተ ወደ 16ኛው መቶ ክፍለ ዘመን ወደ ኋላ፤ የትግሬን ብሔረሰብ በተመለከተ ወደ አምስተኛው መቶ ክፍለ ዘመንና አምስት መቶ ዓመታት ከዚያ ወደኋላ በመመለስ በዚያ ወቅት የነበረውን ሁኔታ ብናየው የዚህ በደል መንስኤ ምን እንደሆነ እንረዳለን፡፡
እንግዳ እቤታችሁ እንዳረፈ አስቡና በእንግደነቱ ሰሞን የሚኖረውን የምትሰጡትን መብት አጢኑት ይህ እንግዳ እቤታችሁ ለዘለቄታው የመቆየት የመኖር ዕድል ቢኖረው ደግሞ ከቤተሰብ አባላት እንደ አንዱ የመቆጠር ዕድል ቢያገኝም ቅሉ በሁሉም ጉዳይ ላይ ግን ልክ ከቤተሰብ አባል አንዱ ሆኖ እንደማይቆጠር እሙን ነው፡፡ ከዚህ አንጻር መሠረታዊ ጉዳዮች በተነሡ ቁጥር የቤቱ ባለቤት “ስንት ለፍቸ ስንት መሥዋዕትነት ከፍዬ ባቀናሁት ቤቴ እኩል ሊገዳደረኝ፣ የባለቤትነት መብቴን ሊጋፋኝ አይገባም” ከሚል አስተሳሰብ የተነሣ እንግደነቱን እንዳይረሳ ለማድረግ፣ እኩል ደራ ደራ ማለቱን ለማቀብ በእንግድነቱ ሊያገኘው ከሚገባው ጥቅም በላይ በቸርነት የተሰጠውን ቤቱን የመጠቀም እንደቤተሰብ የመቆጠር ዕድልን በቂ አድርጎ እንዲያስብ ለማድረግ የተለያዩ ሸንቆጣ ባለቤቱ በእንግዳው ላይ ማድረሱ የማይቀር ይሆናል፡፡ ይህ ሽንቆጣ እንግዳው በእንግድነቱ ዘናትን ባስቆጠረ ቁጥር እንግደነቱ ተረስቶ የቤተሰብ አንዱ አባል እንደሆነ በተቆጠረ ጊዜ ሽንቆጣው ከባድ በደል እንደሆነ ደርጎ የመቆጠር አጋጣሚ ይፈጠራል፡፡ ዛሬ ላይ ተናቅን እንደ ዜጋ አንቆጠርም በማንነታችን እንድናፍር እንድንሸማቀቅ እንደረጋን የሚሉ ወገኖቻችን ይህንን ሁሉ ቅሬታቸውን ዛሬ ላይ አግባብ ሆኖ ብናገኘውም ትላንትና ላይ ግን በፍጹም ሊነሣ አይደለም ሊታሰብ የማይችል ቅሬታ ነበር የእንግድነትን መብት ጠንቅቆ ከመረዳት አንጻር ማለቴ ነው፡፡ እንግዲህ ይህ ሥነ ልቡና ነው እንዲህ ዓይነቱን የሕዝብ ለሕዝብ ግንኙነት የፈጠረው፡፡ ታሪካዊ ዳራ ምክንያት ሰበብ አለው እንዲሁ ከየትም የመጣ አይደለም ለማለት ነው፡፡ የሆኖ ሆኖ አሁን ላይ በመዋለድም በምንም ባለ መብት ያልሆነ የለምና በደም ተሳስሯልና ቅሬታው አግባብነት ያለውና መቀረፍም ያለበት ነው፡፡
article 39ወደ ሁለተኛው መንስኤ ስንሄድ ላይ ላዩን ስናየውን እንገንጠል ለሚሉት ወገኖች እውነት ሊመስል ይችላል፡፡ ጠለቅ ብለን ስናየው ግን ሀብቱ መኖሩ ስስ እውነት ቢሆንም በተለያዩ የተሳሰሩ ምክንያቶች እንገነጠላለን ባዮችን እንደ ሀገር ህልውና አዝይዞ ለመቀጠል ፍጹም የማያስችል ሆኖ እናገኘዋለን፡፡ አሁን በምናውቃት ኢትዮጵያ የችኛውም ክልል ተገንጥሎ እንደ ሀገር ህልውና አግኝቶ ለመኖር የሚያስችል አቅም ዕድል ያለው ክልል የለም፡፡ የኢትዮ ኤርትራን ግጭትና ጦርነት የፈጠረውም ጉዳይ ሌላ ምንም ሳይሆን ይሄው ነው፡፡ ከዚህ አንጻር እኔ በግሌ በተለይ ምሁራን መገንጠልን መፍትሔ አድርገው ያምናሉ ብየ አላስብም፡፡ መገንጠልን መፍትሔ አድርገው የሚያምኑ ምሁራን ካሉ ግን ምሁርነታቸው በጣሙን አጠያያቂ ይሆናል፡፡ እኔ የሚመስለኝ የተማረው ክፍል የመገንጠልን ጥያቄ የሚያንጸባርቀው በመፍትሔነቱ አምኖበት ሳይሆን ለማስፈራራትና በምላሹ መብትን ለማስከበር የመደራደራያ አቅም ለማግኘት፣ ጫና ለመፍጠር ነው ብዬ አምናለሁ፡፡ ዓላማው ለዚህ ቢሆንም እንኳ እልህ ነገሩን ወዳልታሰበ አቅጣጫ ሊወስደው ከመቻሉና ያልተማረውንም ኅብረተሰብ ስለሚያሳስት በማስፈራሪያነትም እንኳን ቢሆን ማንሣቱ ፍጹም ተገቢ ያልሆነና ኃላፊነትም የጎደለው ነው፡፡
ወደ ሦስተኛው መንስኤ ሔድን፡- እንደሚታወቀው ሀገራችን ከጥንት ጀምሮ ዛሬም ድረስ ብዙ ጠላት የሆኑባት ሀገራት ነበሩ አሉም፡፡ ከእነኝህ ሀገራት ጥንተ ጠላት የሆኑቱ ሀገራችን ያለችበት ስልታዊ ቦታና የተፈጥሮ ሀብቷ ህልውናችን ለህልውናቸው አደጋ እንደሆነ በማሰብ ጥቅማቸውን ለማስጠበቅ ጠላት ሲሆኑን፡፡ አዳዲሶቹ ጠላት ሀገራት ደግሞ ከጥቅማቸው ጋራ የዘረኝነት በሽታቸው ተጽእኖ ፈጥሮባቸዋል፡፡ እነዚህኞቹ እንደሰው የማያስቡና ጨካኞችም ናቸው ልክ እነሱ እራሳቸውን ፈለጉት ዘርና የቆዳ ቀለም እንደፈጠሩ ሁሉ ለዚያ የከፋ ጥላቻና ጥቃት ምክንያት ሊሆን የማይችል የማይገባን የቆዳ ቀለምና የዘር ልዩነትን መንስኤ ያደርጋሉና፡፡ የጥቁርን ዘር እንደመገልገያ ዕቃ ቆጥረው ዝንተ ዓለም በቅኝ ግዛት ሲገጥቡት ለመኖር ይፈልጉ የነበሩ ሲሆኑ፤ ሀገራችን ይሄንን ግፈኛ አገዛዝና ኢሰብአዊ ኢፍትሐዊ አስተሳሰብ ከአቅንኦተ ግንኙነት (ዲፕሎማሲ) እስከ ወታደሮቿን በቀጥታ አሰልፋ ቅኝ ግዛትን እንዲያከትምለት ስላደረገች፣ ጥቁር ከነጭ የማያንስ በአንዳንድ ጉዳዮች እንዲያውም የተሻለ የበለጠ መሆኑን በሥልጣኔዋ ማስመስከሯ በጉሮሯቸው ላይ እንደቆመች በመቁጠር ከእርኩሳዊ ቅናትም ጭምር ጥርሳቸውን ነክሰውብን ባጋጠማቸው ዕድል ሁሉ ሲበቀሉን ቆይተዋል ወደፊትም ቢብስባቸው እንጂ ይተውናል ብየ አላስብም፡፡ እንግዲህ እነኝህ ጠላቶቻችን ሁሉም ከድሮ ጀምረው በየራሳቸው ምክንያትና ዓላማ ተሰልፈውብን በየዘመኑ በቀጥታና በተዘዋዋሪ ሲያጠቁን ኖረዋል፡፡ ለእኛ የከፋብን ግን በተዘዋዋሪ ያደረሱብን ጥቃት ነው፡፡ ምክንያቱም በተዘዋዋሪ የሚደርስብን ጥቃት ዜጎቻችንን በክህደት በማጥመቅ ወደ ባንዳነት ቅጥረኛነት በመለወጥ በመሆኑ ከሚደርሰው ጉዳት በላይ በእነዚህ ዜጎች እንደዚያ መሆን በሀገር ላይ በተለያዩ ምክንያቶች ለዘለቄታው ጥሎት የሚያልፈው የችግርና የጦስ መዘዝ የማይነቀል እሾህ የማይድን ነቀርሳ ይተክላልና ነው፡፡
እዚህ ላይ ወያኔን በምሳሌነት ማንሣት እንችላለን፡፡ ወያኔን ማን አሳድጎ ማን ደግፎ ምን ዓላማ አስይዘው ከቆዳ ቀለማቸውና ከስማቸው በስተቀር ኢትዮጵያዊ ቃና ለዛ ማንነት አልባ አድርገው ቀርጸው ጸረ ኢትዮጵያ አቋም አስታጥቀው ማን ለዚህ እንዳበቃቸው መለስ ብሎ ማጤኑ ለዚህ በቂ ምስክር ነው፡፡ ብዙ ሰው የኪነብጀታ (ቴክኖሎጂ) ውጤት እጅግ ያስደንቀዋል፡፡ እኔን እጅግ የሚገርመኝ የሚደንቀኝ ነገር ግን ጠላቶቻችን ወያኔዎችን እንዴት አድርገው ለምንስ ጥቅም አታለው በገዛ ሀገራቸውና ሕዝባቸው ላይ እንደዚህ ዓይነት ጠላት እንዲሆኑ ማድረግ መቻላቸው ነው፡፡ መታየት ያለበት ከገዥ መደብ አለመሆናቸው አይደለም ይሄ ፈጽሞ እንደምክንያት መወሰድ የለበትም ኢትዮጵያ ውስጥ ያሉ ብሔረሰቦች ሁሉ ከ4500 ዓመታት በላይ ለሆነው ታሪኳ፣ ነጻነቷ፣ ሥልጣኔዋ፣ በቀጥታም ይሁን በተዘዋዋሪ እስተዋጽኦ ያላደረገ አንድም ብሔረሰብ የለም፡፡ እንዴትስ ሊኖርስ ይችላል? በመሆኑም የሐገሪቱን ታሪክና ሥልጣኔ የአንድ ብሔረሰብ ብቻ አድርጎ ማሰብ ከቶውንም አይቻልም፡፡ እንዲህ አድርጎ ማሰብ ካልተቻለ በዓለማችን በየትኛውም ሀገር ያሉ ሁሉ ሀገራቸውን ሀገራችን ማለት ባልቻሉ ነበር፡፡
በየትኛውም ሀገር ብንሔድ ለየሀገሩ ሥልጣኔና ህልውና የአንዱ ብሔረሰብ አስተዋጽኦ ጎልቶ መታየቱ አይቀርም እንዲህ በመሆኑ ግን ሌሎቹ ሀገሪቱንና አጠቃላይ እሴቷን የኛ አይደለም እንዲሉ አላደረገም፡፡ በአንዱም ባይሆን በሌላው በቀጥታም ባይሆን በተዘዋዋሪ ለዚያች ሀገር አስተዋጽኦ ማድረጋቸው አይቀርምና፡፡ በመሆኑም ሀገሪቱ ሀገራቸው ናት ታሪኳም ታሪካቸው ነው፡፡ እውነታው እንዲህ በሆነበት ሁኔታ ሰው እንዴት በገዛ ሀገሩ ታሪክ፣ ሥልጣኔ፣ ሉዓላዊነት፣ መለያ፣ ማንነት፣ ክብር፣ እሴት፣ ሀብት ላይ የጥፋት ሰይፍ ታጥቆ ይዘምታል? ጥቅማቸውና ትርፋቸውስ ምንድን ነው? ለዜጎች ከሀገራቸው የበለጠ ጥቅም ዋጋ ክብር ትርፍ ምን ነገር ኖሮ ለዚያ ሊጓጉ ሊቋምጡ ሊታለሉ ቻሉ? ለማንኛውም ጠላቶቻችን ይሄንን ያህል ተሳክቶላቸዋል፡፡ እጣ ፋንታችንም በመዳፋቸው ውስጥ እንደሆነ ያስባሉ ልክ ገመዱን በአንገታችን ላይ እንዳጠለቁና ገመዱን ሸምቅቀው ለህልፈት የማብቃትና ያለማብቃት ጉዳይ በእነሱ ፍላጎት እንደሚወሰንም፡፡ እውን ግን እንደዚያ ይሆን ይሆን?
የመገንጠልን ጥያቄ አግባብነት የሚያሳጡ አመክንዮዎች?
በሀገራችን ችግሮች አሉ ተብሎ መገንጠልን በመፍትሔነት መውሰድና ለመውሰድ መሞከሩ ፍጹም አግባብነት አይኖረውም፡፡ መገንጠል በምንም ተአምር መፍትሔ ሊሆን አይችልም አግተልትሎ የሚያስከትላቸው በርካታ ጥያቄዎች አሉና፡፡ ብቸኛው መፍትሔ በደሉ ቅሬታው ችግሩ እንዲቀር እንዲወገድ ለማድረግ ፍትሕ እኩልነት እንዲሰፍን መታገል ብቻና ብቻ ነው፡፡ በኢትዮጵያ ያለ የኢትዮጵያ ሕዝብ አካል የሆነ ሕዝብ የመገንጠል መብት ሊኖረው የማይችልበት አምስት ዐበይት ምክንያቶች አሉ፡፡
መግቢያችን ላይ ስለ ሀገር ትርጉም ባብራራንበት ወቅት ሀገር በጋራ የሚኖርባት ትልቅ ቤት ነች ማለታችን ይታሳል፡፡ በመሆኑም የዚያ ቤት መፍረስ በየትኛውም ጫፍ ላለ የዚያ ቤት ነዋሪ በቀጥታ ይመለከታዋል ይገደዋል ማለት ነው እንጂ ገንጣዩ ያለበትን አንድ ጫፍ አፍርሼ እወስዳለሁ ስለለ ጉዳዩ የሱ ብቻ ተደርጎ ሊወሰድ አይችልም፡፡ ቤቱ የፈረሰው በአንድ ጫፍ በኩል ይሁን እንጂ የቤቱ መፍረስ በሌላኛው ጫፍ ላለው የቤቱ ነዋሪ ጉዳትና አደጋ ማድረሱ አይቀርምና፣ ሀገሬ ብሎ እዚያ ድረስ እየዘመተ በትውልድ ሁሉ ዋጋ ሲከፍል ኖሯልና፣ መሥዋዕት ሆኗልና፣ ከእነሱ አንዱ የዚያች ሀገር (የጋራ ቤት) ሕዝብ አካል የነበረ ብሔረሰብ መገንጠል ቢፈልግ ሌሎቹ ወይም ከፊሎቹ የማይፈልጉ ይሆናሉና፣ በዚህ ሰዓት በአንድም ወይም በሌላ አጋጣሚ የመገንጠሉ ዓላማ ቢሳካም እንኳ ግጭቱን ወይም ችግሩን ወደ ሌላ ዓይነት የቀውስ ዙር መለወጥ እንጅ የሰላም መፍትሔ ሆኖ አናገኝውምና፣ መገንጠሉን የማይፈልገው ቡድን የተገነጠለውን የሀገሩን ክፍል ለመመለስ መዋጋቱ አይቀርምና፣ የአንድ ጫፍ መፍረስ ከነአካቴውም ለአጠቃላዩ የቤት መፍረስ መንስኤ ይሆናልና በእነዚህ ምክንያቶች አንዱ ሌሎቹን አያገባችሁም ውሳኔው የግሌ ነው ሊል አይችልም ማለት ነው፡፡ በዚያ ቤት ጉዳይ ላይ ሁሉም ነዋሪዎች ይመለከታቸዋል ማለት ነው፡፡ ያ ቤት ለመገንባቱ የሁሉም አስተዋጽኦ ሊኖርበት ግድ እንዳለ ሁሉ በሌላው ጉዳይም እንዲሁ እኩል ይመለከታቸዋል፡፡
በየትኛውም መመዘኛ ቢሆን እራስን ማጥፋት መፍትሔ አይደለም፡፡ ሀገር መገነጣጠል እራስን እንደማጥፋት ይቆጠራል፡፡ ሰው መቸም ካልታመመ የአእምሮ ጤናውን ካላጣ በስተቀር እራሱን አያጠፋም ካልታመመ የአእምሮ ጤናውን ካላጣ በስተቀር እራሱን አያጠፋም፡፡ በመሆኑም ሀገርን እንገነጣጥል የሚሉ አካላት ጤናም እንዲሁ ነውና መብት ሊሆን አይችልም፡፡ ራስን ማጥፋት ወንጀል ነው ወንጀልነቱ እራሱን ለሚያጠፋው ብቻ ሳይሆን እራሱን ሲያጠፋ በዝምታ ለሚመለከተውም ጭምር ነው፡፡ ስለሆነም የአእምሮ ጤና የተጓደለባቸውን ወገኖች ይሁንላችሁ እንዳሻችሁ ልንል አይቻለንም፡፡
በአንድ ወቅት ያለ ሕዝብ በሌላ ወቅት የሚመጣን ሕዝብ መወከል ስለማይችል በእጣ ፋንታውም ላይ መደራደር አይችልም ማለት ነው፡፡ ምክንያቱም የውክልናውን የአግባብነት ጉዳይ ጥያቄ ስለሚያስነሣ፡፡ በአካል የሌለ ግን የሚመጣ ሕዝብ አሁን ያለን ሕዝብ መወከልም ስለማይችል፡፡ አሁን ያለውም አሁን በሌለው ግን በሚመጣው ሕዝብ መወከል ስለማይችል፡፡ ይሄ በሆነበት ሁኔታ ሁለቱም አካላት እኩል መብት አላቸውና አንደኛው በሌላኛው እጣ ፋንታ ላይ እውቅናና ውክልና ባልተሰጣጣበት ሁኔታ ሊወስንበት አይችልም መብት የለውም፡፡ ይህንና መሰል ጉዳዮችን በተመለከተ የየትኛውም ትውልድ መብቱ የሚሆነው የነበረውን ጠብቆ ተንከባክቦ የተቀበለውን እሱም የማስተላለፍ ብቻ ነው፡፡ እሴት መቀነስ አይችልም መጨመር እንጂ፡፡
የመገንጠል ጥያቄ መልስ መገንጠል በፈለገው አካባቢ በሚኖረው ሕዝብ ፍላጎት ከተወሰነና መብት እንደሆነ ከታመነ “ከዚህ በፊት ማንዴላ በሚለው ግጥሜ ላይ እንደገለጽኩት” ለኔ ለብቻዬ የሚለው ጥያቄ የመጨረሻ ማቆሚያ ግለሰብ ላይ ይሆናል እንጅ ብሔረሰብ ላይ ብቻ የሚቆም አይሆንም፡፡ ሀገሪቱ ከ 80 በላይ ብሔረሰብ አላትና ከሰማኒያ ብቻ ተቆራርጣ የምትቀር አይሆንም፡፡ በአሁኑ ወቅት በሀገራችን የተለያዩ ስፍራዎች በጎሳዎች መካከል በግጦሽ መሬትና በውኃ ሳቢያ የኔ ነው የኔ በመባባል እየተጋጨ አየተጫረሰ እንደምናየው የኔ የብቻዬ የሚለው ጥያቄ ወደ ጎሳም ይወርዳል ከጎሳም ወደ ንኡስ ጎሳ ከንዑስ ወደ ንዑስ እያለ ወደ አባወራ ይወርዳል፡፡ በመሆኑም አስተሳሰቡ ከቀላል ችግር ወደ ካባድና ወደ ሰፊ ችግር የሚከት እንጂ መፍትሔና ሰላምን የሚሰጥ አይደለም፡፡ እናም አስተሳሰቡ የተሳሳተ ብስለት የጎደለው የሰው ልጅን የሠለጠነ አስተሳሰብ ወደ ኋላ የሚመልስ ኋላ ቀር አስተሳሰብ ሆኖ እናገኘዋለን፡፡ መግቢያዬ ላይ እንዳልኩት ሀገርን የፈጠራት ሰፊ ፍላጎትና የአቅም ማደግ ነው ብለናልና፡፡
ነባራዊ ሁኔታ ነው፡፡ ምን ማለቴ ነው እገነጣላለሁ የሚለው አካል ማንነት ጉዳይ ነው፡፡ እገነጠላለሁ የሚለው አካል ማንም ቢሆን የመገንጠል ዕድሉ ይሰፋል ማለቴ ሳይሆን በተለይም ደግሞ እገነጠላለሁ የሚለው ብሔረሰብ የኋላ ታሪክ ሲታይ ለዚያች ሀገር እንግዳ ወይም ባዕድ ከሆነ ሁኔታው አስገራሚ ገጽታ ይኖረዋል፡፡ ለምሳሌ ይህንን ጉዳይ በሀገራችን ባለው ተጨባጭ ሁኔታ ብናይ ኢትዮጵያ ውስጥ የመገንጠል ጥያቄ ያነሡትን እራሳቸውን የኦሮሞ ብሔረሰብ ተወካይ አድርገው የሚጠሩትን ኦነግን ብናይ የራስን ታሪክ ጠንቅቆ ካለማወቅ ካልሆነ በስተቀር የኦሮሞ ሕዝብ ለኢትዮጵያ የቅርብ ጊዜ እንግዳ ሕዝብ እንደሆኑ እያወቁ ይኘየንን ጥያቄ ማንሣት እጅግ የዋህነት ነው ልክ ሊሆኑና ጤነኞችም ሊያሰኛቸው የሚችለው ባለቤት አልባ መሬት ቢሆን ነበር፡፡ በመሆኑም ይሀንን ጥያቄ ማንሣቱ አግባብነት አይኖረውም ማለት ነው፡፡
በእነዚህ አምስት ነጥቦች ምክንያት ኢትዮጵያ ውስጥ የመገንጠል ጥያቄን ማስተናገድ ከቶውንም አይቻልም ድርጊቱም መፍትሔ ሳይሆን ጥፋት ነው፡፡
የወያኔ ሕገ መንግሥትና የመገንጠል ጥያቄ
ያደጉ ሀገራት ሕገ መንግሥታት ለምሳሌ የዩ.ኤስ. አሜሪካን ሕገ መንግሥት ያየን እንደሆነ እነኝህን ከላይ የጠቅስናቸውን አምስት ነጥቦች በቅጡ የተረዳ ይመስላል፡፡ ምክንያቱም ስለ ሉዓላዊ ሥልጣን ሲናገር ያውም በሀገሪቱ ላይ ሳይሆን በሕገ መንግሥቱ ላይ ነው “ሕገ መንግሥቱ የተመሠረተው በሕዝቡ በመሆኑ ሉዓላዊነቱም የሕዝቡ እንጂ የነገድ፣ የጎሳ ወይም የሃይማኖት ቡድኖች አይደለም” ይላል ፡፡ ልብ በሉ ሉዓላዊ ሥልጣን አንድ ሕጋዊ ሰውነት ያለው የአጠቃላይ የአሜሪካ ሕዝብ ነው አለ እንጂ በነገድ በጎሳ ስም የተለያየ ህልውና ላላቸው አካላት አላደረገም፡፡ ያውም በሕገ መንግሥቱ ላይ እንጅ በሀገሪቱ ላይ በእጣ ፈንታዋ ላይ ለመወሰን ዕድልና ክፍተት አልሰጠም ምን ያህል ጥንያቄ እንዳደረገ መገንዘብ ይቻላል፡፡ ወደ ወያኔ ሕገ መንግሥት ስንመጣ ግን እጅግ በሚገርምና በሚያሳዝን መልኩ ነገሮችን ጠልቆና ረቆ ያለመረዳት ችግር ያለበት ግልብነትና እንጭጭነት ጎልቶ የሚታይበት ነው፡፡
ሁሉም ሉዓላዊ ሥልጣን በኢትዮጵያ ብሔር ብሔረሰቦች ውስጥ ይሆናል በማለት የብሐረብሔረሰቦችን መብት እስከ መገንጠል ድረስ ነው በማለት የሀገሪቱን ህልውና አደጋ ላይ በመጣልና ለማፍረስ በማሴር ተጀምሮ እስኪጨርስ የሚያወራው ብሐር ብሔረሰቦች እያለ ነው፡፡ የኢትዮጵያ ሕዝብ እንደ አንድ ሀገር ሕዝብ ሕዝብ ተብሎ በወል የሚያስጠራውን ለሀገሩ ያለውን የጋራ የሀሳብ አንድነት አፈራርሶ ሕዝቦች በማለት አንድ ሀሳብና ፍላጎት ለአንድ ሀገር እንደሌላቸው ወይም እንዳይኖራቸው አድርጓል፡፡ ከዚህም በላይ ሀገርን በርእሰ ጉዳይ አንሥቶ ዕውቅና እንኳን ለመስጠት ሀገራችን ብሎ ስለሀገር ለማውራት የተሳነው የሞራል (የቅስም) ብቃትና ድፍረት የጎደለው ቁንጽል ደካማና ባዕድ ሕገ መንግሥት ነው፡፡
በአንድ በኩል የዚህ አስተሳሰብ መሠረት የወያኔ ባልሥልጣናት በተለያዬ ጊዜ ሲገልጹ እንደተደመጡት “የብሔር ብሔረሰቦች መብት እስከመገንጠል የሚለው መብት የተቀመጠው የብሔር ብሔረሰቦች መብት የት ድረስ እንደሆነ ለማሳየት እንጂ እንዲገነጣጠሉ ለማድረግ አይደለም፡፡ መብታቸው እስከተከበረላቸው ጊዜ ድረስ ይሄንን የመገንጠል ጥያቄ የሚያነሣ አይኖርምና መብታቸውን የሚነፍግ ሁኔታ ካጋጠመ ግን ዋስትናቸው ሕገ መንግሥቱ ነው በዚያ መሠረት የመሰላቸውን የመወሰን መብት አላቸው” ይላሉ እነ አቶ መለስ ያልተረዱት ያልገባቸው ነገር ቢኖር አንድ ብሔረሰብ የመገንጠል ጥያቄ ሊያነሣ የሚችለው መብቱና እኩልነቱ ካልተረጋገጠለት ብቻ አለመሆኑን ነው፡፡ መብታቸው ያለ እንከን ቢጠበቅላቸውም እንኳን ይህ የመገንጠል ጥያቄ ሊነሣ መቻሉን ነው፡፡ ለምሳሌ በአንዳንድ ሀገራት ላይ እንደተስተዋለው ሀብት ያለው የተወሰነው የሀገሪቱ ክፍል በመሳሳትና የተሻለ የሕዝባዊ ኑሮ እድገት ላሉበት ለሚኖሩበት የራሳችን ለሚሉት በዚያ አካባቢ ላለ ሕዝብ በመመኘት ከተቀረው የሀገሪቱ ከፍል መገንጠልን የሚፈልጉበት አጋጣሚ በተደጋጋሚ ነዳጅና የከበሩ መአድናት በተገኙባቸው የሌሎች ሀገራት የተለያዩ ቦታዎች የተከሰቱ ጉዳዮች አሉ፡፡ ልዩነትን ካላቻቻሉት በስተቀር መፈጠሩን ማቆም አይቻልም ይህ ገሀዳዊ እውነታ ነው፡፡ እንኳን በሀገር ማለት በጋርዮሽ ውስጥ ይቅርና በአንድ ሰው ውስጥ እንኳን ይፈጠራል ሰው ከራሱ ጋር መግባባት የሚሳነው ጊዜ በርካታ ነውና፡፡ ልዩነት ተፈጥሯዊ ነው፡፡ ይሄንን መግታት ከቶውንም አይቻልም፡፡ ማድረግ የሚቻለው ማቻቻል ነው፡፡
ሠዓሊ አምሳሉ ገ/ኪዳን አርጋው
ሠዓሊ አምሳሉ ገ/ኪዳን አርጋው
የወያኔ ሕገመንግሥት ይሄንን ሀቅ መገንዘብ አልቻለም፡፡ ያውም እኮ ላያደርጉት ነው፡፡ እንግዲህ ለዚህ ነው ልዩነት በተፈጠረ ቁጥር ውሳኔው ያንተ ነው መባል አለበት የሚለው አስተሳሰብ ያልበሰለ ነው ይምለው፡፡ እናም የወያኔ ሕገ መንግሥት የአመለካከት አድማሱ በጣም የጠበበ ግራ ቀኝ የማያማትር ከአድማስ ትዕይንት(scenery) ጀርባ ስለሚኖረውና ስላለው ነገር ሁሉ ምንም የሚያውቀው ነገር የሌለው እንዳለም የማይረዳ ደካማ ሕገ መንግሥት ነው፡፡ እንዲያው ነገሩን አልኩ እንጂ ሕገ መንግሥታቸው የብሔር ብሔረሰቦች መብት እያለ ይደስኩር እንጂ የተባሉት መብቶቻቸው ለአንድም ቀን ቢሆን ተከብሮ አያውቅም፡፡ ወያኔ ህልውናውን የመሠረተውና ያረጋገጠው የእነሱን መብት በመንፈግና እነርሱን ጠርፎ በማሰር ላይ ነውና፡፡ ስለ እውነት ለመናገር ሳንወድ በግድ ቢሆንም ሀገሬ እንዲህ ዓይነት ሕገ መንግሥት እንዲኖራት ስለተደረገች እንዴት ሀፍረትና ውርደት ይሰማኛል መሰላችሁ፡፡
ኢትዮጵያ ለዘለዓለም ትኑር!!!
የወያኔን ከፋፋይ አገዛዝ እናምክን!!!
የኢትዮጵያ ብሄር ብሄረሰብ ሊከበርላቸውና ሊያሳድጋቸው የሚገቡ የተለያዩ የባህልና የታሪክ ቅርሶች ያሏቸውን ያህል በብዙ መንገድ የሚያይዝ የጋራ ታሪክ ቅርስና ዝምድና አላቸው። ልዩነቶቹ ራሳቸው ተጠቃቃሚ ለሆነ የእርስበርስ ግንኙነታቸው ጠቃሚ እንጂ ከአንድ ሀገር ማህበረሰብነታቸውና ከጋራ ህልማቸው ጋር የሚጋጩ የጠብና የግጭት መንስኤዎች አይደሉም። ከጠብና ግጭት ማንኛውም ብሄር ብሄረሰብ ተጠቃሚ አይደለም። ከጠብና ግጭት ጥቅም ይገኛል ብለው የሚያስቡ “ግርግር ለሌባ ይመቻል” የሚለውን የወሮ በላ ፍልስፍና የሚከተሉ የቀን ጅቦች እንጂ የኢትዮጵያ ብሄር ብሄረሰቦች አይደሉም። በወያኔ የግዛት ዘመን የደረሱትን ግጭቶች መፈናቅሎችና የተፈጠሩትን የእርስበርስ ጥርጣሬዎችን ልብ ብሎ ለተመለከተ ሁሉም በአገዛዙ እና በሎሌ የበታች ሹማምንቱ የተፈጠሩ እንጂ አንድም ጊዜ እንኳን ከህዝብ የመነጩ አይደሉም።
የወያኔ ጉጅሌ በአገዛዝ ዘመኑ ሁሉ ብሄር ብሄረሰቦችን ከሚያይዟቸው የጋራ ማህበራዊ ቅርሶችና ህልሞች ይልቅ ካለመታከት ልዩነቶቻችን ላይ ያተኮረ ፖለቲካ እያካሄደ እንዳለ ግልጽ ነው። ከዚህ አልፎም አዳዲስ የእርስበርስ ግጭቶችን እና ጠቦች እንዲፈጠሩ ተግቶ የሚሰራ ከፋፋይ ቡድን ነው። እርስበርሱ መጠራጠርና መፈራራት እንዲሰፍን ልዩ ልዩ ስልቶችን ይቀይሳል። ከአንዱ ብሄረሰብ ተንኳሽ አዘጋጅቶ ሌላው ብሄረሰብ ላይ አደጋ እንዲደርስ ከዚያም ተጠቃሁ የሚለው አጸፋ እንዲመልስ ያደርጋል። የአንዱን ብሄረሰብ መንደርና ንeበረት በእሳት ለኩሶ በሌላው ብሄረሰብ እንዲመካኝ ያድርጋል። አንዱ በአንዱ ላይ እንዲያማርር ከንፈሩን እንዲነክስ ማድረግ ለወያኔ ጉጅሌዎችና ለሎሌዎቻቸው እንደፖለቲካ ጥበብ ከታየ ሁለት አስርት አመታት አልፈዋል። በየትኛውም የሀገራችን አካባቢዎች የተቀሰቀሱ የርስበርስ ጥርጣሬዎችና ግጭቶችን ያሸተተ ሁሉ ወያኔ፣ ወያኔ እንደሚገሙ ያረጋገጠው ጉዳይ ነው።
ወያኔዎች የኢትዮጵያን ብሄር ብሄረሰቦች ከፋፍለውና ከቻሉም አጋጭተው ካልሆነ በስተቀር የዝርፊየ ኢኮኖሚያቸውን መቀጠል እንደማይችሉ አረጋግጠዋል። የኢትዮጵያ ብሄር ብሄረሰቦች የጋራ ጥቅማቸውንና ህልማቸውን ይዘው የተነሱ እለት ወያኔ ያከተመለት መሆኑን ያውቃል። ለዚህም ነው በየክልሉ እና ዞኑ በፍጹም ከሆዳቸውና ጥቅማቸው በላይ ማሰብ የማይችሉ ግለሰቦችን ከየብሄረሰቡ እየመረጠ የሚሾምልን። ወያኔ ነጻ የህዝብ ምርጫ የሚፈራው ለዚህ ማረጋገጫ ነው፡፡
የወያኔ ጉጅሌዎች ከጊዚያዊ ጥቅም በዘለለ ማሰብ ስለተሳናቸው እንጂ ይህ አካሄዳቸው ለራሳቸውም ለዘለቄታው የማይጠቅም መሆኑን ዘንግተውታል። በልዩነታችን ላይ መጫወት ማለት በእሳት እንደ መጫወት የማይመስላቸው ለዚህም ነው። ይህ የተጀመረው እሳት ራሳቸውንም አይምርም።
ድል ለኢትዮጵያ ህዝብ!!!
የጥላቻው እሳት ቆስቋሹን ያቃጥለው!!!
የትግል መሰረቱን ጎጥ ላይ ያደረገ፣ የእድገት ልኩን ዘረፋ ላይ ያዋለና የእውቀት ጥጉን ውሸት ላይ የመሰረተ እንዴትም ሆኖ የነጻነት ታጋይ አይሆንም። ይልቁንም በሕዝብ ጫንቃ ላይ ተንፈራጥጦ እንዲኖር የክፋት መርዙን ይረጫል እንጂ። ምንም በሁኔታዎች አስገዳጅነት ቢተጣጠፍ እንኳ ኢትዮጵያዊነትን ከፍ የማድረግ አቅም ስለሌለው ሕብረት ያስፈራዋል፣ ነጻነት ያጥወለውለዋል፣ አንድነትም ያስበረግገዋል። ኢትዮጵያ ለወያኔ ትርፍ እስካስገኘች ድረስ እንደምትታለብ ላም ነች። ከዚያ በላይ ወያኔዎች ሀገራዊ ራዕይ የሚባል ነገር የላቸውም።
እንደ ሀገርና እንደ ሕዝብ ያለብንን ፈተና በጎጥ መነጽር አይተን በጥላቻ ክርክር ተጯጩኸን በግል ስምና ዝና ጦዘን ልንወጣው ፈጽሞ አይቻለንም። በተለይ ከቅርብ ጊዜ ወዲህ እለት በእለት የምንመለከተው ሁነት እያሳየን ያለው ተፋቅረንና ተደጋገፈን መኖር የሚገባን ወገኖች ተናንቀን ስንነካከስ ነው። ጃስ እያሉ የሚያናክሱን ደግሞ እንግሊዝ በቀበረው የእርስ በእርስ መተላለቂያ ፈንጂ፣ ጣልያን በቀመመው የጎሳ ክልል መርዝና በየሃገሩ እሳት ጭረው በሚወጡት ለጥቅማቸው ሲሉ ምንም ከማድረግ በማይመለሱ ሀያላን እገዛ እየተጠቀሙ ወደ ጥፋት የሚነዱን ደናቁርቶች ናቸው። ሰሞኑን በወያኔዎችና ለወያኔ የጥላቻና ፕሮፖጋንዳ ሰለባ በሆኑ ቡድኖች ወገኖቻችንን በዘር ለማናከስ እንደ አበደ ውሻ የሚክለፈለፉ በዝተዋል። የሰከነ የአንድነት ድምጽ እንዳይደመጥ ወያኔ ከፍተኛ አፈና በሚያደርግባት ኢትዮጵያ ጎልቶ የሚደመጠው የደንቆሮ ጩኸት ነውና አማራጭ ድምጽ እንዲደመጥ ካላደርግን ህዝባችን ሊወናበድ ይችላል።
በከሃዲና ስግብግብ የአፍሪካ መሪ ተብዬዎች ውክልና የሀገርና አህጉር ሀብትና ቅርስ በንግድ ሽፋን ዘረፋ ላይ ለተሰማሩ ሀገር በቀልና የወጪ ከበርቴዎች እየተቸረ ነው። በዘመናዊ ትምህርት ስም የሀገር ፍቅርንና ለህዝብ የመቆም አስፈላጊነት ችላ እንድንል የተበረታታን ተልፈሰፈስንና የማንነት መሰረታችን ተናግቶብን ብዙ ዘመነኞች እኛንና ህዝባችንን ለብልቦ የሚፈጀንን የጥፋት እሳት እንደ ደመራ እያጨበጨብን ከበን እያየነው እንገኛለን። ኢትዮጵያ በታሪክዋ አይታ የማታውቀው በሌላውም አለም ያልተለመደ አይነት አሳፋሪ የሀገር ጠላት የሆነ የዱርዬ ስብስብ መንግስት ነኝ እያለ አገሪቱን ለእቁብ ወይንም ለቤት ኪራይ ገንዘብ እንዳጠረው ነጋዴ ሃገራችንን በርካሽ ዋጋ እየቸበቸበ ይገኛል።
በሀገር ልማት ስም ከየአቅጣጫው የሚሰበሰበው የብድር መአት በኛ ዘመን ቀርቶ በልጅ ልጆቻችን ጊዜም ተከፍሎ አያልቅም። የተበደሩት ገንዘብ ግን ግማሹ ወደ መጣበት ሀገር ተመልሶ በሌቦቹ ባለስልጣናት ስም በተከፈቱ የባንክ ሂሳቦች ገቢ ተደርጎ የጨረቃ ሚሊየነሮችን መፍጠሪያ ሆኗል። ኢትዮጵያ የኢኮኖሚ መሰረትዋና አብዛኛው ህዝቡዋ የሚተዳደርበት ሁኖ ሳለ የእርሻ መሬቶች ለውጪ መንግስታትና ግለሰቦች እየተቸበቸቡ ነው። ይህ ደግሞ ኢትዮጵያውያንን ዛሬ መሬት አልባ ነገ ደግሞ አገር አልባ ያደርጋቸዋል።
የዛሬዎቹ መሪ ተብዬዎች መሬትን መያዝ ሀገርን መቆጣጠር ነው ብለውም ነው መሬት የመንግስት ነው የሚሉት። አዎን ዛሬ መሬት የትግራይ ማፊያዎች ሀብት ነው። ያሻቸውን ለማድረግ የያዙት ታንክና ላውንቸር መብት አጎናጽፎአቸዋል። የተቀረው ኢትዮጵያዊ መሬትም መብትም የለውም! ሌላ ቀርቶ ነገና ከነገወዲያ ጤፍ፣ ስንዴና ገብስም የትላልቅ ‘ምርጥ ዘር’ አምራቾች ሸቀጥ እንጂ ለዘመናት መሬቱንና የሰብሉን ዘር ሲንከባከብ የኖረው ገበሬው ሀብት አይሆኑም። ገበሬው የዘርና ማዳበርያ ዋጋ መክፈል እያቃተው መሬቱን ጥሎ ለማኝና ስደተኛ እንዲሆን እያደረጉት ነው። ይህን አደገኛ አኪያሄድ አሁን ካልገደብነው ኢትዮጵያ የምትባል አገር መኖሩዋ አጠራጣሪ ይሆናል። ይህም ባይሆን እንኩዋን ህዝባችን በገዛ ሀገሩ ለጥቂት የውጭና የውስጥ ዘራፊ ባለሃብቶች ጪሰኛ ይሆናል። ወያኔዎች ያለመታከት ለዚህ መከራ እያሰናዱን ነው እኛም ዛሬ ለነሱ ደባ ተመቻችተንላቸው ለዘመናት በጎሳ በቁዋንቁዋም ይሁን በሀይማኖት ሳንለያይ አብረን መኖራችንን ችላ በማለት በጎጥ አንሰን በመንደርም እየተከፋፈልን አገርም ማንነትም ለሚያሳጡን አረመኔዎች በራችንን በርግደን እንዲያምሱን ልንፈቅድ አይገባም።
ዛሬ በራሱና በወገኖቹ ላይ በሚደርሰው ሰቆቃ በማዘን “ራሴን ጠላሁ” “በኢትዮጵያዊነቴ አፈርኩ” የሚለው የተቆጣ ሕዝብ ብዙ ነው። ይህን ቁጣውንና ዱላውን ለሰቆቃው ምንጭ በሆነው ወያኔ ላይ እንዳያሳርፍ እነ ስብሃትና በረከት ስምኦን ጸቡን በአማራና ኦሮሞ፣ በክርስትያንና ሙስሊም ወ.ዘ.ተ. መካከል ለማስቀረትና ለኛው የእልቂት ድግስ መደገስ ከጀመሩ ብዙ ቆዩ። ያለመንግስትና ያለፖሊስ ተከባብሮ የመኖር ድንቅ ባህልን ያዳበረውን ሕዝብ ዛሬ አናቁረውት ሌብነት ቅጥፈትና ዘረፋ የብልጥ መንገድ እንደሆነ እየሰበኩ ወደ ንቅዘት የሚመሩት እነዚሁ የወያኔ ወሮበሎች ናቸው። የማይሞላ ከርስና ባዶ ጭንቅላት ያላቸው የየብሄረሰቡ ተወካይ ተብዬዎች ደግሞ አንደ ተወጠረ ከበሮ አለቆቻቸው ትንሽ ኮርኮም ወይም ኮርኮር ሲያደርጉዋቸው ይጮሀሉ። በጎሳና ሀይማኖት ህዝባችን አይነጣጠልም ያልነው እውነት እንዲሆን እርስ በራሳችን እንዳንፋጅ ሁላችንም የወያኔን የጥላቻ ቅስቀሳ ልማክሰም የድርሻችንን የምናደርግበት ጊዜ ዛሬ ነው። ይሄ አያገባኝም ወይም አይደርስብኝም ማለት ከሌሎች ተሞክሮ አለመማር ይሆናል።
ሩዋንዳውያን አንድ ሚሊየን ያህል ወገኖቻቸው በግፍ ከተፈጁ በሁዋላ በህልማችንም በእውናችንም ጉዋደኛ ለጉዋደኛ ጎረቤት ለጎረቤት እየተራረድን እንዲህ ያለ ክፋት እኛው በኛው ላይ እንፈጸማለን ብለን አናስብም ነበር ሲሉ መስማት የተለመደ ነው። ከበርካታ አመታት በሁዋላ በሕዝብዋ ላይ የተፈጸመው ጭፍጨፋ አሁንም ድረስ ድባቡ አልጠፋም። አሁንም ድረስ እያስታወሱ የሚያለቅሱ አሉ። በዚሁ ግፍ ምክንያት በርካቶች አይምሮአቸውንም ስተዋል። በቁንጅናዋ ተማርኮ በጸባይዋ ተመስጦ አፍቅሮ ያገባትን ሚስቱንና የልጆቹን እናት የጥላቻ ቅስቀሳ ሰለባ በመሆን በቆንጨራ ጨፍጭፎ እንዲገድል የተደረገ ሰው በህይወት ቢኖርም ሰው መሆን አይችልም። ሺህ ይቅርታ ሺህ ሱባዔ ሺህ ቅጣት ያንን ጤና መልሶ ሊሰጠው አይችልም። የጥላቻውን መርዝ መጀመሪያ የረጩትና እሳቱን ያራገቡት ግን ለመግዛት እንዲመቻቸው አንዱን ከሌላው አሳንሰው እርስበርስ እንዲጠላላ በማድረግ የኖሩት ቅኝ ገዢዎቹ ናቸው። ከነጻነት በሁዋላም ጎረቤት በጎረቤቱ ላይ በጥላቻ እንዲነሳሳና ያ ሁሉ እልቂት እንዲፈጸም እጃቸው አለበት የሚባሉት መስቀል ይዘው ክርስትና ሰባኪ ነን የሚሉ ነጮች መሆናቸው ይነገራል።
ኤርትራ “በነጻ አውጪዎቹ” ስትያዝ ለብዙ አመታት እዚያው ኑሮ መስርተው ሃብት አፍርተው የነበሩ ኢትዮጵያውያን “አያት ቅድም አያቶቻችሁ ከዚህ አይደሉም” እየተባሉ በጎሳ ጥላቻ ቤተሰባቸው እንዲፈርስ ተደርጎ ባዶ እጃቸውን በባዶ እግር እንዲባረሩ ወደባህርም እንዲገፉ የተደርጉትን ልናስብ ይገባል። ከመሀል አገርም ከሌላ ብሄረሰብ ተወላጆች ጋር ተጋብተው ይኖሩ የነበሩ ኤርትራውያን እራሱ ኤርትራው በሆነው በመለሰ ዜናዊ “የአይናቸው ቀለም ካላማረን እናባርራልን” የሚል የ እብሪት ፖለቲካ ቤተሰባቸውንና ንብረታቸውን በትነው ከሀገር እንዲወጡ እንደተደርጉ ልናስታውስ ይገባል። ዛሬም ከየቦታው የሚፈናቀሉት ወገኖቻችንን ቁጣ ልናስብና ይህ ቁጣም ወዴት ሊያመራ እንደሚችል ማሰቡ ከሚጠብቀን አደጋ እንድንጠነቀቅ ያመቻቻል።
አማራው ከኦሮሞው ቢጣላ ገላጋይ ሆነን እንቆማለን የሚሉት የትግራይ ተገንጣይ ቡድን አባላትና ደላሎቻቸው ሕዝብን ከሕዝብ ለማናከስ ደፋ ቀና የሚሉት እሳቱ ቢነሳ እነርሱ የሚተርፉ መስሏቸው ነው። የተገፋው የተጨቆነውና በደል በቃኝ የሚለው የኢትዮጵያ ሕዝብ ጠላቱን ለይቶ አውቆ የጥላቻ እሳት እየቆሰቆሱ ያሉትን በተባበረ ክንድ ሊደቁሳቸው እንደሚችል የተገነዘቡ አይመስልም። ለዚህም ነው ሕዝቡ ቁጣውን ወደነዚህ አረመኔዎች ሊያዞርና ሴራቸውን ሊያከሽፍ የሚገባው ዛሬ ነው ጊዜው እየረፈደም ነው የሚል ጥሪ ከየአቅጣጫው የሚስተጋባው። በርካቶች ወደ ጥላቻ ወጥመዳቸው እንዳይገቡ እነዚህን ክፉዎች መንጥሮ ማውጣት ለነገ የማይባል አስቸኩዋይ የህልውና ጥያቄ ነው። መሰረታዊው ልዩነት ሀገር በሚዘርፉ፣ በሚያፈርሱና እልቂት በሚደግሱት ወያኔዎችና በተቀሩት ኢትዮጵያውያን መካከል እንጂ በተለያዩ ብሄረሰቦችና ሃይማኖት ተከታዮች መሀከል አይደለም።
በምዕራቡ ሀገራት በሚሰበክው የመድብለ ፓርቲዎች አስፈላጊነት ምክንያት ኬንያ በርካታ ፓርቲዎች ማቋቋም ባሰበችበት ወቅት ፖለቲከኞቹ መራጮቻቸውን ፍለጋ በየጎጡ መሄዳቸው ያስከተለው ከባድ ቀውስ ዛሬ የሚታወስ ነው። አሜሪካ መድብለ ፓርቲ ብላ አስጨንቃ ከያዘችን ብለው እነዚያው የቀድሞ ፖለቲከኞች ወደየዘመዶቻቸው ሲሄዱ ይህ ሊያስከትል የሚችለውን አደጋ ያገናዘበ አገናዝቦም መፍትሄ የሰጠ አልነበረም። ብዙ ፓርቲዎችም ተፈጠሩ ግን የጎጥ ፓርቲዎች ሆኑ። ይህን በመከተልም አሰቃቂ የሆነ አደጋ ሰላማዊ ተብላ በምትታወቀው አገር ተከሰተ። የአንድ ሀገር ልጆች መሆናቸውን ከመቅጽበት ዘንገተው ኩኩዩ ሉዎ እየተባባሉ በገጀራና በቀስት እርስበርስ ይገዳደሉ ጀመር። ኬንያውያንም እኛ ሰላም ወዳዶችና የጎሳ ፖለቲካ ወደ ጽንፍ የማይወስደን ነን የሚል ጽኑ እምነት የነበራችው ቢሆኑም የጥላቻው ቅስቀሳ ለጊዜያው የፖለቲካ ጥቅም ከተለኮሰ በሁዋላ በሀገራችን እናያለን ብለው ያልገመቱት የጥላቻ ግድያ ሲፈጸም ለመመልከትና ተሳታፊም ለመሆን ተገደዱ። ። የረገፉት ረገፉ የተፈናቀሉትና ከሞት የተረፉት ግን ዳግም የሰላም እንቅልፍ አይኖራቸውም። ኬንያ የበርካታ የውጭ መንገስታትና ድርጅቶች የፖለቲካና የኢኮኖሚ ጥቅም የሚያገኙባት ሀገር በምሆኑዋ ዓለም ትኩረት ሰጥቶት እንደ ኮፊ አናን ያሉ መፍትሄ አፈላላጊዎች ሁሉ ተረባርበው እሳቱን ለጊዜውም ቢሆን አበረዱት።
የኛዋ ኢትዮጵያ ግን እኛው ካላዳንናት በእሳቱ ላይ ነዳጅ የሚጨምር እንጂ እሳት የሚያበርድላት ብዙ እንደማይኖር ልብ ልንል ይገባል። ወራሪን በማሸነፍ የሚገኝ ነፃነት የሚያስከፍለውን መስዋትነት በኩራት ልንሸከም የሚገባን እኛው ኢትዮጵያውያን ነን። አዋሳኝ አገሮችም በአብዛኛው ለኛ መዳከምና መበታተን ተግተው የሚሰሩ ናቸው። የጎጠኞችና የባንዳዎች ብቸኛ ሕልም ደግሞ ምንም ያክል ትሁን ስልጣንና ሀብት ማጋበስ ብቻ ነው። በጎጥ የጀመረ ፀብ በእንጭጩ ካለተቀጨ መንደርና ቤተሰብ ድረስ ይዘልቃል። የትግራይ ተገንጣይ ቡድን ሚሊየኖችን አስፈጅቶ ስልጣኑና ሀብቱ ግን የተገደበው በጥቂት ቤተሰብና መንደር ላይ መሆኑ ሩቅ የማይወስድ ምሳሌ ነው። የትግራይ ሕዝብ በጥቅሉ ከሌላው በተለየ ደስተኛ እንዳልሆነ ማየት ትምህርት ነው። በመከባበርና በመተሳሰብ ለልጆቻችን ለልጅ ልጆቻችን ህልውናና ነፃነት ስንል የአቅማችንን እንስራ ኢትዮጵያንም እናድናት።
በጎጠኞች መርዘኛ ሴራ ኢትዮጵያዊነት አይረታም!
ኢትዮጵያ በነፃነትዋ ተከብራ ለዘለዓለም ትኑር!
Tuesday, March 4, 2014
የአድዋ ድልና ትሩፋት ፈተናዎቹ

በእርግጠኝነት ኢትዮጵያዊ ልብ ላለው ሰው ሁሉ ስለ አድዋ ድል ሲሰማና ሲያወራ ልቡ በኩራት ይሞላል መንፈሱ ይነቃቃል፡፡ ኢትዮጵያዊ ብቻም አይደለም በየትኛውም ዓለም ያለ በቅኝ ግዛት ቀንበር ፍዳ ያየ የትኛውም የሰው ዘር ጭምርም እንጅ፡፡ ይህን አንጸባራቂ ድል መላው የኢትዮጵያ ሕዝብ በአንድነት ተሰልፎ ካስመዘገበ እነሆ ነገ የካቲት 23 ቀን 2006ዓ.ም 118 ዓመቱን ይይዛል፡፡ ይህንን ድል ለመቀዳጀት ፈተና የነበሩት ነገሮች ምን ምን ናቸው? ለመሆኑ ይህ ድል እንዴት ተገኘ ? የዚህ ታላቅ ድል ትሩፋቶችስ ምን ምን ናቸው? የዚህ ድል ጠላቶች እነማን ናቸው? ይህ ድል እንዴት ይጠበቃል? ብዙ ቢባልለት ከማይበቃው ከአድዋ ድል እነዚህን ነጥቦች ብቻ ነጥለን ለማየት እንሞክራለን፡፡
ዐፄ ምኒልክ ምታ ነጋሪት ክተት ሠራዊት ብለው ፋሽስት ጣሊያን በዘመነ ዐፄ ዮሐንስ 4ኛ ከነበረበት አልፎ የትግሬ ገዥ የነበሩትን ዐፄ ዮሐንስ 4ኛ ከእሳቸው ቀጥለው እንዲነግሡ በማሰብ ሊሞቱ በሚያቃትቱበት ወቅት ወራሸ ነው ለእኔ ያደረጋችሁትን ሁሉ ለእሱም አድርጉ በማለት ተናዘውላቸው የነበሩትን ራስ መንገሻን ድል አድርጎ ሠራዊታቸውን ከበተነ በኋላ አልፎ መላዋን ሀገራችንን ቅኝ ለመግዛት ወደ መሸገባቸው ቦታዎች ወደ አንባ አላጌ፣ መቀሌ እንዳሥላሴና አድዋ ከመዝመታቸው እነዚያን አኩሪ ድሎች ከማስመዝገባቸውና ታሪክ ከመሥራታቸው በፊት እነኝህን ድሎች እንዳንቀዳጃቸው የሚያደርጉ እጅግ ከባባድ ፈተናዎች ተጋርጠውብን ነበር፡፡ የአድዋን ድል በሌሎች ሀገራት ከተገኙት ድሎች ልዩ የሚያደርገውም ይሔው ነው፡፡ እነዚህ ፈጽሞ ሊታለፉ የማይቻሉ መሰናክሎችን ታልፎ የተገኘ ድል በመሆኑ፡፡
የአድዋን ድል ለመቀዳጀት አያስችሉ የነበሩት ፈተናዎች ምን ምን ናቸው፡-
- የከብት እልቂት፡- ፋሺስት ጣሊያኖች ኢትዮጵያን ቅኝ ለመያዝ ሲያስቡ ቅኝ ገዥዎች በአፍሪካና እስያ በቀላል ግጭት ቅኝ ሀገር መያዝ እንደቻሉ ሁሉ በኢትዮጵያ ይህ መልካም እድል እንደማያጋጥማቸው ጠንቅቀው ዐውቀውት ነበር፡፡ በመሆኑም ጦርነት መግጠማቸው የማይቀር ከሆነ የኢትዮጵያንና የመንግሥቷን አቅም ለማዳከም የሚያስችል ስልት ነደፈ ከስልቶቹ አንዱም የሀገሪቱ ሀብት መሠረት የሆነውን ግብርናዋን ማሽመድመድ መጉዳት ነበር፡፡ ይህንን ሲያስቡ ግብርናዋን ለመጉዳት ማድረግ የሚችሉት ነገር ሆኖ ያገኙት የከብት ሀብቷን መጨረስ ነበር፡፡ ይህንን ለመፈጸም ሲባል ከህንድ ሀገር ሶስት የታመሙ ከብቶችን በምጽዋ በኩል አስገብተው ከደማቸው እየወጉ የኞቹን ደኅናዎቹን ከብቶች በመውጋት አጋቡባቸው በሽታውም በአጭር ጊዜ ተዛምቶ ከኢትዮጵያም አልፎ አጠቃላይ የቀጠናውን ከብት ፈጀው፡፡ ውጤቱም ፋሽስቶቹ ከጠበቁት እጅግ የበዛ ሆኖ በሀገራችን ታሪክ ታይቶ የማይታወቅ ‹‹ክፉ ቀን›› በመባል የሚታወቀውን ረሀብና ችጋር አመጣ፡፡ የሚበላ ነገር ጠፍቶ ዋልካ አፈርና ሳር ቅጠሉ ሁሉ የተበላበት ዘመን ነበር፡፡ ሕዝቡ ደቀቀ አለቀ ሀገሪቱ ተሽመደመደች፡፡
- የስንቅና ትጥቅ (logistics) ዝግጅት እጅግ ውስንነት፡- ፋሽስት ጣሊያን በወቅቱ ኃያላን ከሚባሉ የአውሮፓ ሀገራት አንዱ ነበረ፡፡ እንደ ኃያልነቱም ከ20 ሺ በላይ ለሆነው ላሰለፈው ጦሩ ዘመናዊ መሣሪያ በነፍስ ወከፍ ከማስታጠቁም ባሻገር ሠራዊቱ በወጉ የተደራጀ ዘመናዊ የውትድርና ሥልጠና የወሰደ ባጠቃላይ ከበቂ በላይ የስንቅና ትጥቅ ዝግጅት የነበረው ነበር፡፡ በእኛ በኩል የነበረው ደግሞ ባጋጠመው የረሀብና አስከፊ ችጋር የደከመ ሠራዊት ከመሆኑም በላይ ከፍተኛ የሆነ የስንቅና ትጥቅ አቅርቦች ችግር ነበረበት፡፡ በወቅቱም ሠራዊቱ ነፍሱን ለማቆየት በቀን እጅግ መጥኖ ከሚቀምሳት በየ አገልግሉ ቋጥሮ ከያዛት ጥቂት ዳቦቆሎ፣ የደረቀና የሻገተ ቂጣ፣ ቆሎና በሶ የመድኃኒት ያህል ጥቂት ጥቂት የሚቀምስ ሠራዊት ነበረ እንጅ የስንቅ አቅርቦቱን አስቦ በየ ዕለቱ አብስሎ የሚያቀርብለት አካል አልነበረም፡፡ ሰራዊትም ሲባል ሐበሻ እንዲያው በተፈጥሮው ተዋጊ በመሆኑ እንጅ ሊገጥመው እንደተዘጋጀው ጠላቱ ሠራዊት በወጉ የወሰደው የውትድርና ትምህርት ጨርሶ አልነበረም፡፡ የታጠቀው መሣሪያም ቆመህ ጠብቀኝ በሚባል የሚታወቁ ኋላ ቀር መሣሪያ ሆኖ ይሄንንም ቢሆን የያዙት ከሠራዊቱ እጅግ ጥቂቶቹ ነበሩ የተቀረው ግን የያዘው ጦርና ጋሻ ጎራዴ ነበር፡፡ ይሔም አይጠቅምም ማለት ሳይሆን በጦር በጎራዴና በጋሻ ውጊያ የሚደረግበት ዘመን አልፎ ከሩቁ ጠላትን መልቀም ማስቀረት የሚቻልባቸው ከመድፍ እስከ መትረየስ ያሉ ዘመናዊ መሣሪያዎች የወጡበት ዘመን በመሆኑ ለሚደረገው ጦርነት የጦር የጎራዴ እና የጋሻ ጥቅምና አገልግሎት እጅግ በጣም ውስን ሆኖ ነበር፡፡ ጦርነት በጦር በጎራዴ ይደረግ የነበረበት ዘመን ለእኛ እጅግ የቀና የበጀና የሰለጠም ነበር፡፡
- የባንዶች ሚናና የጠላት የመከፋፈል ስልት፡- ፋሽስት ጣሊያን የኢትዮጵያን ሠራዊት ለማዳከም ከተጠቀመበት ስልት
ሌላኛው ባላባቶችንና መሳፍንቱን እስከ ራሶች ድረስ እንዲከዱ በማድረግ ከጎኑ ማሰለፍ ነበር፡፡ ጥቂት የማይባሉትንም ማስካድ ችሎ ነበር ነገር ግን እነዚህ የከዱና ከነሠራዊታቸው በባንድነት የተሰለፉ መኳንንት የጠበቁትንና የፈለጉትን አቀባበልና መስተንግዶ እንዳላገኙና እንደማያገኙም ሲገባቸው የዐፄ ምኒልክ ይቅር ባይነት ዋስትና ሆኗቸው ብዙዎቹ ተመልሰዋል፡፡ ይሁን እንጂ እነኝህ ከድተው የነበሩ ሹማምንት መመለሳቸው የእውነት ከልብ ነው ወይስ ለተልዕኮ? የሚለው ጉዳይ ለወገን ሠራዊት በወቅቱ እጅግ አንገብጋቢ ጥያቄና እውነቱን ለመረዳት ከመቸውም አጋጣሚ በበለጠ አምላክነትን የሚያስመኝ፤ ሥጋት ጥርጣሬውም እረፍትና እንቅልፍ የሚነሳ አምኖ ለማሰለፍም ለመተውም ያስቸገረበት ጉዳይ ሆኖ ነበር፡፡ - የፋሽስት ጣሊያን ጦር መሽጎ ያለ መሆኑ፡- ጦርነት በሚደረግበት ወቅት ጦርነት ከሚያደርጉት ባላንጣ አካላት አንደኛው ምሽግ ይዞ የሚጠብቅ ከሆነ ጦርነቱ ለአጥቂው ወይም ምሽግ ላልያዘው ክፍል እጅግ ከባድና አስቸጋሪ የሚያስከፍለው ዋጋም ከመሽገው አካል ጋር ሲነጻጸር በጣም የሚበዛ መሆኑ የማይቀር ነው፡፡ እኛንም ያጋጠመን ይሄው ነበር በሶስቱም ቦታዎች የጠላት ጦር ምሽጉን በሚገባ ገንብቶ ከምሽግ ማዶም በባዶ እግሩ የሚጓዘውን አርበኛ ሠራዊት እንዲቆራርጥ በጠርሙስ ስብርባሪና በጦር ችካሎች ከዚያም በፈንጂ የታጠረ ምሽግ ውስጥ ሆኖ አድፍጦና መሽጎ ይጠብቅ የነበረ ጦር ከመሆኑ የተነሣ የጠላትን ጦር ከዚህ ምሽጉ ለማስወጣት ምን ያህል መሥዋዕትነት ሊጠይቅና ሊያስከፍል እንደሚችል መገመት ይቻላል፡፡ እንኳንና ተመጣጣኝ ትጥቅ ሳይያዝ ቢያዝም እንኳ ሁኔታው እጅግ ከባድ ነው በዚህ ላይ የእኛ ጦር ዘመናዊ የውጊያ ስልት ካለመማሩ ጋር ተያይዞ ተኝቶ መሬት ላይ በመሳብ መተኮስን እንደ ነውርና ፈሪነት አድርጎ የሚቆትር በመሆኑ ደረቱን ሰጥቶ በከፍተኛ ድፍረትና ወኔ ይዋጋ የነበረ ጦር ከመሆኑ ጋር ተያይዞ መሥዋዕትነቱን እጅግ የከበደ አድርጎት ነበር፡፡ የሚገርመው ነገር ግን ከነዚህ ነባራዊ ሁኔታዎች አኳያ ከጦርነቱ በኋላ የደረሰብን የሟችና ቁስለኛ መጠን በጠላት ሠራዊት ከደረሰው እምብዛም የሚበልጥ አልነበረም፡፡
- የህክምና አገልግሎት ችግር፡- እንዲህ ዓይነት የሕዝብ እንቅስቃሴ በሚደረግበት ወቅት ወረርሽኝ ይከሰታል፡፡ ወረርሽኝ ሲከሰትም ለዚህ ጉዳይ ቀድሞ የተዘጋጀ ህክምና ከሌለ ከባድ ጥፋት አስከትሎ ያልፋል፡፡ የወገን ጦር ይሔንን አደጋ መከላከል የሚችልበት አቅምና ዝግጅት አልነበረም ሌላው ቀርቶ ቁስለኛን እንኳን ማከም የምንችልበት መድኃኒትና ባለሙያ አልነበረንም ሁሉም ለየራሱ ሐኪም ነበረ፡፡ አስተናግር ቅጠሉን ጨምቆ አዘጋጅቶ ይዞት የመጣውን ቁስሉ ላይ እያፈሰሰ እርስ በራሱ ለመተካከም ይሞክራል እንጅ ይሔንን ጉዳይ የሚከውን የህክምና ቡድን አልነበረም፡፡
እንግዲህ እነዚህና ሌሎች ሊታለፉ የማይችሉ እንደተራራ የገዛዘፉ ከባባድ ደንቀራዎችን ፈተናዎችን በእግዚአብሔር ቸርነት በሐበሻነት ጽናት እናት አባቶቻችን አልፈው ነው የአንባላጌውን፣ የመቀሌውን፣ በመጨረሻም የአድዋን ድል ለመቀዳጀት የቻሉት፡፡ የአድዋ ድል በሌሎች ዜጎች ዘንድም በከፍተኛ አድናቆት የሚደነቀው የሚከበረውም ከዚህ የተነሣ ነው፡፡

ለመሆኑ ይህ ድል እንዴት ሊገኝ ቻለ?፡- ለድሉ መገኘት ትልቁ ድርሻ የእግዚአብሔር ረድኤት ቢሆንም እግዚአብሔር ሲሠራ በምክንያት ወይም መሣሪያ የሚያደርገው ነገር መኖሩ አይቀርምና ለእናት አባቶቻችን ቁርጠኝነትን፣ ጽናትን፣ መጨከንን ሰጥቶ ከቶውንም የማይታለፉትን ፈተናና መከራን አስተናግዶም በእነሱም ደክሞ ደቆ የነበረ ሕዝብ ተሰባብሮ ተነሥቶ እንዲህ ዓይነት አስደናቂ ድል ለማስመዝገብ በቃ፡፡ እንዲህ ዓይነቱን ድል ለማስመዝገብ ሐበሻ ሆኖ መገኘትን የግድ ይጠይቅ ነበር አደረግነውም፡፡ በመሆኑም “ነፃነት ወይም ሞት” “ባሪያ ሆኖ ከመኖር ነፃ ሆኖ መሞት” የሚለው የጨከነ መርሑ ከፊቱ የተደቀኑ ግዛዙፍ ፈተናዎችን መሰናክሎችን ከነ አካቴው ከግምት ውስጥ እንዳያስገባ አድርጎት በከፍተኛ ቁርጠኝነትና ጽናት በመዋጋቱ ድሉን ሊያገኝ ቻለ፡፡
የዚህ ታላቅና አንጸባራቂ ድል ትሩፋቶች ምን ምን ናቸው? ይህ ታላቅ ድል ከእኛም አልፎ ለመላው ዓለም ጭቁኖች በርካታ ትሩፋቶችን አበርክቷል ከእነዚህ በርካታ ትሩፋቶቹ ጥቂቶቹን ለመጥቀስ ያህል፡-
1. የቀለም ልዩነትን መሠረት ያደረገው የብቃት ደረጃ ልዩነት አስተሳሰብን ፉርሽ መሆኑን ማረጋገጥ ችሏል፡፡ ከዚህ ድል አስቀድሞ ጥቁር ሲባል ሰብአዊ እሴት አልባ፣ ለባርነት የተፈጠረ፣ ሥልጣኔ የማይገባው አድርገው ያስቡት ነበር፡፡ ከዚህም አልፈው ተናጋሪ እንስሳ እያሉ ይገልጹት ነበር፡፡ ጥቁሮቹ እናት አባቶቻችን ግን ፈጽሞ ሊታለፉ የማይቻሉ ፈተናዎችን አልፈው ለክብራቸው ለነፃነታቸው፣ ለሉዓላዊነታቸው የማይችሉት ነገርም እንኳን ቢሆን አንችለውምና ምን እናድርግ ብለው ክብራቸውን፣ ነፃነታቸውን፣ ሉዓላዊነታቸውን ለድርድር ሳያቀርቡ ለሰብአዊ ክብራቸውና ለማንነታቸው ታይቶ በማይታወቅ ቀናኢነት በየትኛውም የዓለም ክፍል ያለ ማንኛውም ዓይነት የሰው ዘር አደርገዋለሁ ብሎ ሊሞክረው ቀርቶ ሊያስበው በማይችለው ሁኔታ በግሩም ችሎታና የአጨራረስ ብቃት ከውኖ በማሳየቱ ጥቁር እንዲህ እንዲህ ነው እየተባለ ዝቅ ተደርጎ ይቆጠርና ይታይ የነበረው አስተሳሰብ የተሳሳተ መሆኑን የግዳቸውን እንዲያምኑ አድርጓል፡፡
2. የነፃነት ትግልን አነቃቅቷል ቀስቅሷል፡- ጥቁር አፍሪካዊያን ለአምስት ምእተ ዓመታት ያህል በግፈኛ ነጮች ሲሰበክላቸው የኖረውን የጥቁርን ተገዥነት ወይም ለአገልጋይነት መፈጠር አምኖ ተቀብሎ ሰጥ ለበጥ ብሎ የመገዛትን አስተሳሰብ አዳብሮ ወደ አውሮፓና አሜሪካ እየተጋዘ እየተሸጠ እየተለወጠ ይገዛ ያገለግል ነበር፡፡ ሐበሾቹ ጥቁሮች አድዋ ላይ ያበሩላቸው ፀሐይ ግን ይሄንን የጨለመ አስተሳሰብ ጠራርጎ በማጥፋቱ የነጻነት ትግልንና የነፃነት ታጋዮችን በየስፍራው በየአቅጣጫው እንዲቀጣጠል አድርጎ እነሆ ዛሬ ላይ ያን ሁሉ ግፍ በጥቁርነቱ ብቻ ይጋት የነበረው የሰው ዘር ነጻነቱን አረጋግጦ ቢያንስ በገዛ ሀገሩ እንኳን እንደ ሰው መኖር የሚችልበትን ሁኔታ መፍጠር እንዲችል አብቅቷል፡፡

3. የተረሳውን ታሪካችንን አስታውሷል፡- ሐበሻ እንደሕዝብና እንደ ሀገር ከማንም የቀደመ የሥልጣኔና የመንግሥት ታሪክ ያለውና የነበረው ሕዝብ ነው ይህ ግን በወቅቱ በነበረው አስገዳጅ ችግር ሳቢያ ከዐፄ ፋሲል ጀምሮ ለረጅም ጊዜ ቆይቶ በነበረው ዝግ መመሪያ (closed policy) ምክንያት ዓለም እኛን እኛም ዓለምን ረስተን ተረሳስተን ስለነበረ ዓለም በየጊዜው መረጃውን እያደሰ እንዳወቀን እዲቀጥል ማድረግ ሳንችል ቀርተን ነበር፡፡ የአድዋ ድል ግን ዓለም ስለኛ ያለውን መረጃ ካጎረበት እያወጣ እንዲያወራ እንዲህ እኮናቸው እንዲህእኮ ነበሩ እያለ እንዲያወራ አድርጎታል፡፡ ያወሩልን ይፅፉልን ከነበረው ታሪኮቻችን የሚበዛው እኛም እንኳን እራሳችን የማናውቃቸው ናቸው፡፡
4. የሕዝባችንን አንድነት አጽንቷል፡- የጠላት ወረራ ለመኳንንቶቻችንና ለመሳፍንቶቻችን ትልቅ ትምህርትን ሰጥቷል፡፡ በአንድነት የመቆምን አስፈላጊነት የአንድነትን ጥቅም በሚገባ አስገንዝቧቸዋል፡፡ ከዚያ አስቀድሞ ከዘመነ መሳፍንት ጀምሮ በመሳፍንቱና በባላባቶች ዘንድ የየራሳቸውን ጎጥ እንደ ሀገር በመቁጠር የየራሳቸውን ‹‹ሀገር›› የመመሥረት የማይጠቅምና ኋላ ቀር አስተሳሰብ ያስቡ ነበር፡፡ ይህን የትም የማያደርስ አስተሳሰብ ለማጥፋት ዐፄ ቴዎድሮስን እጅግ አድክሟል፡፡ በዐፄ ቴዎድሮስ እጅ ያደጉት ዐፄ ምኒልክ 2ኛም የዐፄ ቴዎድሮስ 2ኛ ሕልም ገብቷቸው ስለነበር ጥረታቸውና ሁኔታዎች ፈቅደውላቸው የዐፄ ቴዎድሮስን ሕልም ለማሳካት ችለዋል፡፡ የአድዋ ድልም ለመሳፍንቱ የማይረሳ ትምህርትን ስለጣለላቸው ከዚያ በኋላ አስቀድሞ የነበረው ዓይነት የመሳፍንት አስተሳሰብ እንዳይኖር አድርጓል፡፡
5. ለቀጣይ ትውልድ ታሪክ እንዴት እንደሚሠራና እንደሚጠበቅ ምሳሌነቱን ትቶ አልፏል፡- ሀገራችን ከ4500ዓመታት በላይ የመንግሥት ታሪክ አላት እንደ ሀገር ከቆመችበት ጊዜ ጀምሮ ነጻነቷን ለመንጠቅ ተደጋጋሚና አደገኛ ፈተናዎችን አሳልፋለች፡፡ እነዚሁ ጣሊያኖች በቀደመው ስማቸው ሮማዊያን ከቄሳሮች ዘመን ከሁለት ሽህ ዓመታት በፊት ጀምረው ሲፈታተኑን ኖረዋል፡፡ የአድዋ ድል እናት አባቶቻችን የዚህችን ሀገር ነጻነት እንደምን ባለ መሥዋዕትነት አስጠብቀው እንደቆዩና ይህ ረጅም ታሪኳ እንዴት እንደተሠራ የቅርብ ጊዜ ምሳሌነት የተወ ድል ነው፡፡ በደካማ ጎን መግባት የሚችሉበት ጠላቶቻችን ግን የትግል ስልታቸውን በቀጥታ ከሚተኮሰው አፈሙዝ ወደ ተለየ ዓይነት በመለወጥና ባንዶችን በማሠማራት የአድዋ ድል ከተወልን ምሳሌነት ልንማርና እኛም የድርሻችንን ታሪክ ልንሠራ የምንችልበትን ዕድል አጥበውት ሀገርን፣ አንድነትን፣ታሪክን፣ ነጻነትን፣ ሉዓላዊነትን፣ ክብርን መሠረቱ ያላደረገ የየግል ዓላማና አስተሳሰብ አራጋቢዎች አድርገውን አንድነታችንን አደጋ ላይ ጥለውታል፡፡በዚህ ረገድ እየተሳካላቸው ይገኛል፡፡ ፈጣሪ ይቅደምልን እንጂ የዚህ ውጤት ደስ የሚያሰኝ አይሆንም፡፡
6. የታሪክ ሀብትን ትቶልናል፡- አንዲት ሀገር ዜጎቿ ጠንካሮች ከሆኑ ሁለቱም ሀብቶች ይኖሯታል ቁሳዊና መንፈሳዊ ሀብቶች ታሪክ መንፈሳዊ ሀብት ነው፡፡ ታሪክ መነቃቃትን የሚፈጥር ታላቅ ኃይል ነው፡፡ ቁሳዊ ሀብትም የመፍጠር ዐቅም አለው፡፡ ሀገራችን ኢትዮጵያ ሁለቱም ሀብቶች ነበሯት፡፡ ነበሯት ማለቱ ግድ ሆኗል አሁን ላይ ቁሳዊው እንደሌለ ግልጽ ቢሆንም መንፈሳዊው ሀብታችንም ራሱ ድራሹ እንዲጠፋ በከፍተኛ ትጋት እየተሠራበት ነውና ነበረን ማለቱ ይቀላል፡፡ ሊገባኝ ያልቻለው ነገር ግን ከዚህ ማን ምን ዓይነት ትርፍ አንዴት ሆኖ እንደሚያገኝ፤ ጥቅሙ ምን እንደሆነ ነው፡፡ ለሕዝቡ ልጠይቅ የምሻው አንድ ጥያቄ አለኝ የእናት አባቶቻችን ሀገር ኢትዮጵያ በዓለም ውስጥ ከነበሩት አራት ኃያላን መንግሥታት አንደኛዋ ነበረች፡፡ ይህች ሀገር ዛሬ የዓለም ጭራ ደሀዋ ሀገር ሆናለች ለምን? ይህ እንዴት ሲሆን ቻለ? እነሱ ጋር የነበረው ጠንካራ ጎን ይህችን ደሀና ደካማዋን ኢትዮጵያ ከፈጠርነው ከእኛ ጋር ያለው ደካማ ጎን ምንድን ነው?
7. ዕውቅናና መከበርን አትርፎልናል፡- ይህ ድል የማያውቁን አንዲያውቁንና ሀገር ለሀገር ለሚደረግ ግንኙነት ተመራጭ እንድንሆን አድርጓል፡፡ የሚያውቁንም እንዲያከብሩን አድርጓል፡፡ ባጠቃላይ ወዳጅ ብቻ ሳይሆን ጠላትም እንዲሁ በተመሳሳይ ሳይወድ በግድ ዕውቅናና ክብር እንዲሰጥ አድርጎታል፡፡ የዛሬን አያርገውና ከዚያ በኋላ ለመጣችው ኢትዮጵያም ሞገስን አጎናጽፎ በዲንሎማሲው (በአቅንዖተ ግንኙነቱ) ተደማጭ ተከባሪ እንድንሆን አድርጓል፡፡
8. ለመሪነት ሚና ተመራጭ እንድንሆን አድርጓል፡- ይህ ድል በሰጠን ዕውቅና ሳቢያ በተለያየ አቅጣጫ የፈጠራቸው በቅጭ ግዛት ይማቅቁ የነበሩ ሀገራት የፀረ ቅኝ ግዛት እንቅስቃሴ በሚያደርጉበት ወቅት ይህንን እንቅስቃሴያቸውንና ትግላቸውን እንድንደግፍ እንድናስተባብር ለመጠየቅ አስገድዷቸዋል፡፡ ሀገራችንም ይህንን ትግል የመምራቱን ታሪካዊ ኃላፊነት ሙሉ ለሙሉ በማመን ሀገራቱ ነጻ እስኪወጡ ድረስ የራሷን የጦር መሪዎችንና ተዋጊዎችን በማሰለፍ ጭምር ትግሉን ስታግዝ ስታስተባብር የተጣለባትንም አደራ በሚገባ ተወጥታለች፡፡ ለቀድሞው የአ.አ.ድ ለአሁኑ አ.ህ እና ለሌሎች አህጉራዊና ዓለም ዓቀፋዊ ድርጅቶች መቀመጫነት እንድትመረጥ ያበቃትም የዚሁ ድል ትሩፋት ነው፡፡
9. ሰንደቅ ዓላማችንን እንድንወስን አብቅቷል፡- በእርግጥ ከአድዋ ድል አስቀድሞም የሀገራችን ነገሥታት ቀይ ቢጫ አረንጓዴ ወይም አረንጓዴ ቢጫ ቀዩን ሰንደቅ ይጠቀሙ እንደነበር ይታወቃል፡፡ ነገር ግን በአዋጅና በይፍ ዕውቅና ተሰጥቶት ሀገራችንንና ሕዝባችንን እንድትወክል የተደረገው ዐፄ ሚኒልክ አድዋ ላይ ይህንን አንጸባራቂ ድል ከገኙ በኋላ እዚያው አድዋ ላይ አዋጅ አስነግረው ከእንግዲህ ወዲህ ይህ ቀይ ቢጫ አረንጓዴ ሰንደቅ የኢትዮጵያ ሰንደቅ ዓላማ ሆኗልና ከክብር በላይ ክብርን፣ ከፍቅር በላይ ፍቅርን፣ ከአለኝታነት በላይ አለኝታነትን ስጧት ብለው በማስነገራቸው ይፋዊ ሰንደቃችን ሆና ለመቀጠል ቻለች፡፡

እንግዲህ በአጭር እንቋጨው እንጅ የአድዋን ትሩፋት እንዲህ በቀላሉ ዘርዝሮ የሚጨረስ ጉዳይ አይደለም፡፡ በመቀጠል የአድዋ ድል ጠላቶች እነማን ናቸው? የሚለውንና ይህንን ቅርስ እንዴት ልንጠብቀው እንችላለን? የሚለውን በአጭር በአጭሩ ዐይተን እንቋጭ ፡፡
የአድዋ ድል ጠላቶች እነማን ናቸው?
የእድለቢስነት ጉዳይ ሆኖ ሀገራችን ኢትዮጵያ ለጠላት የታደለች ሀገር ነች፡፡ በዚህች ሀገር በየትኛውም ሀገር ታይቶ በማይታወቅ መልኩ ለቁጥር የሚያታክቱ ጦርነቶች ከውጭና ከውስጥ በሚፈጠር ቀውስ ሰበብ አስተናግዳለች፡፡ ይህች ሀገር ካስተናገደችው የጦርነቶች ብዛት አንጻር በታሪኳ በአማካኝ ከ10 ዓመታት ያለፈ የሰላምና የእፎይታ ቆይታ ዓይታ አታውቅም፡፡ ተአምር የሚሆንብኝ ነገር ቢኖር ይህንን ያህል የአውዳሚ ጦርነት ዓይነት ያስተናገደች ሀገር ደብዛዋ አለመጥፋቱ የሥልጣኔና የታሪክ አሻራዎቿም ጥቂቱንም ያህል ቢሆን መቆየት መቻላቸው ነው፡፡ አሁን ላይ አስቀድሞ የነበሩን ጠላቶቻችንም ሆኑ ሌሎች አዳዲስ ቢኖሩ ጥቃታቸውን እየፈጸሙብን ያለው እንደቀድሞው በወረራ ሳይሆን በመሀከላችን ልዩነቶች እንዲፈጠሩ በማድረግና እርስ በእርስ በማናቆር በማፋጀት ሆኗል፡፡ ይሄም ይዞላቸዋል፡፡ አርቀውና አስፍተው ማሰብ የማይችሉ ወገኖቻችን የሀገራችን የሕዝብ ለሕዝብ ግንኙነት ምንም እንኳን እንከን የለሽ ነበር ማለት ባይቻልም በየትኛውም የዓለም ክፍል ከነበረው እጅግ የተሻለው እንጅ ተመሳሳይ እንኳን እነዳልነበረ፤ በበቂ ምክንያትና አማራጭም በመታጣቱ ለሀገር አንድነትና ህልውና ሲባል አንዳንድ የማያስደስቱን ነገሮች መደረጋቸውን መገንዘብ ማስተዋል የተሳናቸው ደናቁርት ለእነኝህ ጠላቶቻችን መሣሪያ በመሆን የሀገራችንንና የሕዝባችንን ህልውና ገደል አፋፍ ላይ አድርሰውታል፡፡ ዛሬ ላይ በየትኛውም የዓለም ክፍል ላይ ያሉ የባርነትና ጭቆና ቀማሽ የነጻነት ደጋፊና አቀንቃኞች የሚኮሩበትን የሚያከብሩትን የሚያደንቁትን የአድዋን ድልና ያንን ድል ያስገኙልንን አርበኞች እዚህ ኢትዮጵያ ውስጥ ሆነው በጥላቻ የሚመለከቱ መጥፋት መረሳቱን የሚፈልጉ ለዚህም የሚሠሩ ዜጐች ለማየትና ለመስማት ደርሰናል፡፡ መፍትሔው ምንድን ነው ትላላቹ?
ይሄንን ቅርስ እንዴት ልንጠብቀው እንችላለን?
ይሄንንና ሌሎች ቅርሶቻችንን ሀብቶቻችንን ታሪኮቻችንን ልንጠብቃቸው የምንችለው ለነዚህ ሀብቶቻችን አንድ ዓይነት መግባባት ሲኖረን ሀብቶቹ በሚገባ የመጠበቅ እድል ይኖራቸዋል፡፡ አእምሮ ካለን እዚህ አንድ ዓይነት መግባባት ላይ ላንደርስ የምንችልበት እንድም ምክንያት አይኖርም፡፡ ወደራሳችን ወደ ውስጣችን እንመልከት፡፡ እያደረግነው ያለውን ነገር ከመፈጸሙ በፊት የሚገኘውን ትርፍና ኪሳራ እንመዝን፡፡ እንዲህ እንድናደርግ እንድንናቆር እንድንባላ የሚመክሩን የሚገፋፉን የሚደግፍን ሀገራት በታሪካቸው ከእኛ የከፋ የእርስ በእርስ ሰብአዊ መብት ገፈፋ ዝጋብ (record) ያለባቸው ሀገራት ናቸው፡፡ ነገሥታቶቻቸው ሲያርፉ ጠባቂ እያሉ ሰዎችን ከነነፍሳቸው ግራና ቀኝ ይቀብሩ የነበሩ ናቸው፡፡ የሰው ልጆችን ከአራዊት ጋራ እያታገሉና እያስበሉ ለመዝናኛነት ይጠቀሙ የነበሩ ሀገራት ናቸው፡፡ ይህ ተሞክሮ በሀራችን ፈጽሞ ኖሮ አያውቅም፡፡ ዛሬ ላይ እነሱ እንኳን አንድ ዓይነት መግባባት ደርሰው በአንድነት ቆመው ለሀገራችው ጥቅሞች በአንድ የተሰለፉ ሆነዋል፡፡ እነሱ ለዚህ የበቁ እንደነዚህ ያሉ ዘግናኝና ኢሰብአዊ ድርጊቶችንና አስተሳሰቦችን ዓይተን የማናውቀው እኛ ኢትዮጵያዊያን እንዴት አንድ ዓይነት መግባባት ላይ ለመድረስ ያቅተናል? ለሀገርና ለሕዝብ እስካሰብን ጊዜ ድረስ ፈጽሞ አያቅተንም፡፡ ሀገርንና ሕዝብን ጠልተንና ንቀን ባንዳነትን ከመረጥን ግን መቸም ጊዜ ቢሆን ልንግባባና የሰላም አየር ልንተነፍስ አንችልም፡፡
Subscribe to:
Comments (Atom)






